ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ

ዜና: በአማራ ክልል በሰላም እጦት በተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ስራ ከ25 በመቶ በላይ አለመሠራቱን ክልሉ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 6/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭት እና ሰላም እጦት የግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ይገኛል ሲሉ የክልሉ የግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ገለጹ።

በተፈጠረው ችግር በርካታ ሥራዎች ወደኋላ መቅረታቸውንም የገለጹት ሃላፊው በተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ ሥራ ከ25 በመቶ በላይ አለመሠራቱንም አስታውቀዋል።

በየአካበቢው የሚገኙ የግብርና ተቋማት በጽንፈኛ ኃይሉ ጉዳት ደርሶባቸዋልም ያሉት ዶ/ር ድረስ በቀሪ ወራት በሕዝብ ንቅናቄ የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ መሥራት ይጠበቃል ብለዋል። የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የስምንት ወራት የሥራ አፈጻጸም እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ባካሄደው ምክክር መድረክ ላይ ሃላፊው የተፈጥሮ ሀብት ልማት ሥራ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ወደኋላ መቅረቱንም አንስተዋል፡፡

በመኸር ወቅት 5 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማረስ እንደታሰበም ያስታወቁት ሃላፊው ባለፈው ዓመት ያጣነውን ነገር ዘንድሮ ማካካስ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

በአማራ ክልል የማዳበሪያ እጥረት ችግር እንደማይኖር የጠቆሙት ዶ/ር ድረስ 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ መግባቱንም ገልጸዋል፤፡ የእቅዱ 45 በመቶ የሚሆነው ማዳበሪያ እየገባ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ አሁን ያለው አቅርቦት በጣም ጥሩ ነው ያሉት ኃላፊው የቀረበውን ወደ አርሶ አደሮች ማሰራጨት ላይ ሥራዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡

አርሶ አደሮች ራሳቸውን እያደራጁ ማደበሪያ እንዳይዘረፍ የማድረግ ሥራ እንዲሠሩም ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ባለፈው ዓመት ጀምሮ በአማራ ክልል ታይቶ የማይታወቅ የማዳበሪያ ዝርፊያ መታየቱን የተናገሩት ኃላፊው ከክረምት ጀምሮ ከ33ሺህ በላይ ኩንታል መዘረፉንም ገልጸዋል፡፡ ዘረፋው ትክክል ያልሆነ እና የተሳሳተ አካሄድ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡ አርሶ አደሮች ይህንን ተግባር ማውገዝ እንደሚጠበቅባቸውም ገልጸዋል፡፡

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የማዳበሪያ አቅርቦትን በጥንቃቄ ማሰራጨት እንደሚገባ አሳስበው ካለው ማዳበሪያ አንጻር የተሰራጨው ማዳበሪያ ብዙ አለመሆኑን ማመላከታቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button