ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: የፕሪቶርያ ስምምነት ዋነኛ ጉዳዮች ባለመፈጸማቸው ከፌደራል መንግስቱ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን መተማመን እየሸረሸረው ይገኛል – ህወሓት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም፡- በአፍሪካ ህብረት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የፕሪቶርያ ስምምነት አፈጻጸምን በገመገመው ስብሰባ ዙሪያ ህወሓት ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያ ስምምነት ዋነኛ ጉዳዮች ባለመፈጸማቸው ከፌደራል መንግስቱ ጋር ተፈጥሮ የነበረውን መተማመን እየሸረሸረው ይገኛል ሲል አስታውቋል።

ትግራይን በመወከል የፕሪቶርያውን ስምምነት የፈረመው ልዑክ ስምምነት ላይ ከተደረሰበት ዕለት ጀምሮ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ሪፖርት አቅርቧል ያለው የህወሓት መግለጫ የተሰሩ ስራዎችን እና ያጋጠሙ ችግሮችን በዝርዝር ማቅረቡን አመላክቷል።

በአወንታዊነት በዝርዝር ከቀረቡት ነጥቦች መካከል ሙሉ በሙሉ ተኩስ መቆሙ፣ በክልሉ የአገልግሎት ተቋማት ስራ መጀመራቸው፣ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን የእርዳታ አቅርቦት መኖሩ ይገኙበታል ብሏል።

በክልሉ ላይ አሁንም ሁሉም መንገዶች አለመከፈታቸው እና ከበባው ሙሉ በሙሉ አለመነሳቱ፣  የስምምነቱ የተወሰነው ክፍል በተሟላ መልኩ አለመፈጸሙ፣ አብዘሃኛዎቹ ወሳኝ እና ታላላቅ የስምምነቱ ጉዳዮች አለመፈጸማቸውን በአሉታዊነት በዝርዝር መቅረቡንም አስታውቋል።

በስምምነቱ መሰረት በትግራይ በኩል እንዲፈጸሙ ከተቀመጡት መካከል ከባድ መሳሪያዎችን ማስረከብ እና የተወሰኑ መካከለኛ የጦር መሳሪያዎችን ከማስረከብ ጀምሮ አብዘሃኛው ተፈጽሟል ሲል ህወሓት በግምገማ መድረኩ ከትግራይ በኩል በቀረበው ሪፖርት መገለጹን ጠቁሟል።

መግለጫው በተጨማሪም ከመሳሪያ እርክክቡ ጎን ለጎን መፈጸም የነበረበት የኤርትራ ሰራዊት እና የአማራ ታጣቂ ሀይሎችን ከትግራይ ግዛቶች የማስወጣቱ ስራ አልተፈጸመም ሲል አስታውቋል፤ ከ40 ከመቶ በላይ የሚሆነው የትግራይ ግዛት አልተመለሰም ብሏል። በዚህም ምክንያት ከአንድ ሚሊየን የሚልቀው የትግራይ ተፈናቃይ ወደ ቀየው እንዲመለስ ማድረግ አልተቻለም የሚል ሪፖርት መቅረቡንም ጠቁሟል።

በስምምነቱ መሰረት የ2014 ዓ.ም መደበኛ እና የፕሮጀክት በጀት እስካሁን ባለመለቀቁ የመንግስት ሰራተኛውን የተከማቸ ደመወዝም ይሁን የጡረተኞችን ደመወዝ መክፈል አለመቻሉን አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአጠቃላይ የስምምነቱ አበይት ጉዳዮች አለመፈጸማቸውን ያስታወቀው የህወሓት መግለጫ በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለው መከራ እንዲቀጥል ከማድረጉ ባለፈ ከፌደራል መንግስቱ ጋር የነበረንን መተማመን እየሸረሸረው ይገኛል ብሏል።

በስትራቴጂ ግምገማው በፌደራል መንግስቱ በኩል የቀረበው ሪፖርት በአመዛኙ በሀገሪቱ የተለያዩ ባለስልጣናት ሲንጸባረቅ የነበረው ሀሳብ ነው የቀረበው ሲል ገልጿል።

በፌደራል መንግስቱም ይሁን በህወሓት በኩል አሁንም ለፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ያለንን ታማኝነት አረጋግጠናል ሲል ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button