ዜና

ዜና፡ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የፕሪቶሪያው ስምምነት "እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር" ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 18/ 2016 ዓ/ም፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር “በአካባቢው ማህበረሰቦች መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት በጥልቀት እየተከታተሉ” መሆኑን ገልጸው፤ የፕሪቶሪያው ስምምነት “እንዲከበርና ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር” ጥሪ አቀረቡ።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህመት ይህን ያሉት፤ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባባሪያ ቢሮ፤ አላማጣ፣ ኦፍላ አና ዛታን ጨምሮ በደቡብ ትግራይ ዞን በተቀሰቀሰው አለመረጋጋት ከ50 ሺህ በላይ ዜጎች ወደ አማራ ክልል መፈናቀላቸውን ባወጣታው ሪፖርት መግለጹን ተከትሎ ዛሬ ባወጡት መግለጫ ነው። 

በአካባቢው አለመረጋጋት የተቀሰቀሰው፤ በደቡብ ትግራይ ዞን የተቋቋሙትን አስተዳደሮች ለማፍረስ የፌዴራል መንግስት ጥረት ማደረጉን ተከትሎ ነው።  አካባቢው፤ በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በአማራ ክልል የታጠቁ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የነበር ነው።

የህብረቱ ሊቀመንበር በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ፤  ለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት “በጣም አዋጭ አካሄድ”  የሆነው “የፖለቲካ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ ያቀረቡ” ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ በህወሃት እና ፌደራል መንግስቱ መካከል የተደረሰው ስምምነት “እንዲከበር እና ሙሉ ለሙሉ እንዲተገበር ጠይቀዋል። 

በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ቀን፤ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች በአካባቢው የተፈጠረው ውጥረት እንዲረግብ እና ሁሉም አካላት የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣ ወደ ህብረተሰቡ የመቀላቀል እና መልሶ የማቋቋም ጥረትን እንዲያፋጥኑ እንዲሁም ንጽሃን እንዲጠበቁ ጥሪ ማቀረባቸው ይታወሳል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button