ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ማይክ ሀመር በናይሮቢ እና አዲስ አበባ ለአስር ቀናት ከየሀገራቱ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 23/2015 ዓ.ም፡- በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በናይሮቢ እና አዲስ አበባ ከነሃሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ ጳጉሜን 3 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ለአስር ቀናት ጉብኝት እንደሚያደርጉ ተገለጸ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ሀመር በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከሀገሪቱ ባለስለጣናት ጋር በሰላም ስምምነቱ አተገባበር ዙሪያ ቀጣይነት ያለው ውይይት ያደርጋሉ። በተጨማሪም በአማራ ክልል እና በኦሮምያ ክልል በመካሄድ ላይ ያለውን ግጭት በውይይት መፍትሔ ለማስገኘት እና ንጹሃን በግጭቱ ሰለባ እንዳይሆኑ ከለላ በሚያገኙበት መንገድ ዙሪያ እንደሚመክሩ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው አመላክቷል።

ማይክ ሀመር በጉብኝታቸው ከአፍሪካ ህብረት፣ ከኢጋድ እና ከአለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ጋርም በመገናኘት በቀጠናው ጉዳይ በተለይም በሱዳን ጉዳይ እንደሚመክሩ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ መግለጫ ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button