ዜናፖለቲካ

ዜና: እልባት ያላገኙ የወሰን ጉዳዮች በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት የመቀስቀስ እድል አላቸው ሲል የአሜሪካ የስለላ ተቋማት ሪፖርት አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም፡- የፕሪቶርያው ስምምነት በኢትዮጵያ አንጻራዊ ሰላም ቢያሰፍንም እልባት ያላገኙ የወሰን ጉዳዮች ሀገሪቱን ወደ ዳግም ጦርነት ሊያመሯት ይችላሉ ተባለ።

መጋቢት 2 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ የሆነው አመታዊው የአሜሪካ የደህንነት ማህበረሰብ የስጋት ምዘና ሪፖርት እንደሚያሳየው የፕሪቶርያው ስምምነት በኢትዮጵያ የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ማስቆም ቢችልም እልባት ባላገኙ የወሰን ጉዳዮች ሳቢያ በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት ሊቀሰቀስ ይችላል ሲል አስጠንቅቋል።

በተጨማሪም ሪፖርቱ ኢትዮጵያ በርካታ የውስጥ ግጭቶችን እያስተናገደች መሆኗን ጠቁሞ በሀገሪቱ በሚገኙ ብሔሮች መካከል ውጥረት መኖሩን አመላክቷል፤ በንጹሃን ላይ ግፍ የመፈጸም አደጋ አንዣቧል ብሏል።

ባሳለፍነው አመት ሚያዚያ ወር ላይ በአማራ ክልል የተጀመረውን ግጭት ያስታወሰው ሪፖርቱ በፋኖ ታጣቂ ሀይሎች እና በሀገሪቱ መከላከያ ሰራዊት መካከል በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት አመቱን ሙሉ መቀጠሉን እና ወታደራዊ ግጭትን እያስተናገደ ይገኛል ሲልም ገልጿል።

ከቀናት በፊት በአፍሪካ ህብረት አዘጋጅነት በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የተደረሰውን የፕሪቶርያ ስምምነት አፈጻጸም የሚገመግም ስብሰባ በአዲስ አበባ መካሄዱን መዘገባችን ይታወሳል።

ከቅርብ ግዜያት ወዲህ በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር በኩል በስምምነቱ አፈጻጻም ዙሪያ በመሰጠት ላይ ያሉ መግለጫዎች በሁለቱ መካከል ያለው ልዩነት መስፋቱን የሚያመላክቱ ተደርገው ተወስደዋል።

ስትራቴጂያዊ ግምገማው ከተጠናቀቀ በኋላ ህብረቱ ባወጣው መግለጫ የፕሪቶርያው ስምምነትነ የፈረሙት የፌደራል መንግስቱ እና ህወሓት ከቅርብ ግዜያት ወዲህ የሚታየውን የሰፋ ልዩነት ለማጥበብ ስለተደረገው ጥረት ያለው ነገር የለም።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በህገመንግስቱ እና በፕሪቶርያው ስምምነት መሰረት የትግራይ ግዛታዊ አንድነት ሙሉ በሙሉ አለመከበሩ፣ በትግራይ መሬት ላይ የሚገኙ የአማራ ታጣቂዎች እና የኤርትራ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ አለመውጣታቸው እና ከቀያቸው የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎች ወደ ቤታቸው አለመመለሳቸው የልዩነቶቹ ዋነኛ ነጥቦች ሁነው በመቅረብ ላይ ይገኛሉ። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button