ዜና

ዜና፡ በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ከ180 በላይ ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸውን ነዋሪዎች ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 4/2016 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ባሳለፍነው ሳምንት “በፋኖ ታጣቂዎች” የተፈጸመው ጥቃት መቀጠሉን እና ከ180 በላይ የወረዳው ነዋሪዎች ታግተው ገንዘብ እየተጠየቀባቸው መሆኑን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናገሩ።

በሳለፍነው ሳምንት ሃሙስ የካቲት 28/ 2016 ዓ/ም “የፋኖ ታጣቂዎች” በደራ ወረዳ፤ ጂሩ ዳዳ፣ ወሬን ገብሮ እና ማንቀታ ዋሪዮ በሚባሉ ሶስት ቀበሌዎች በፈጸሙት ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መሞቸውን እና በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል። 

ስሙ እንዲገለጽ ያልፈለገ የወሬን ገብሮ ቀበሌ ነዋሪ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ሃሙስ ዕለት በታጣቂዎቹ የተፈጸመው ጥቃት መቀጠሉን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል። ነዋሪው፤ “ጂሩ ዳዳ፣ ወሬን ገብሮ እና ማንቃታ ዋሪዮ ቀበሌውች ጥቃቶች ቀጥለዋል፤ ከቀበሊዎቹ 186 ሰዎች ታግተዋል” ብሏል።  

ሰዎቹ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ታግተው እንደሚገኙ የገለጸው ነዋሪው፤ ከታጋቾቹ መካከል ሁለት ነፈሰ ጡር ሴቶች ታግተው ባሉበት ቦታ መውለዳቸውን ተናግሯል። 

አክሎም “ታጣቂዎቹ ታጋቾቹን ለመልቀቅ በአንድ ሰው ከ150 ሺህ እስከ 200 ሺህ ብር እየጠየቁ ነው” ብሏል።  

አዲስ ስታንዳርድ ይህን ጉዳይ በተመለከተ የደራ ወረዳ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ፤ አለባቸው ኃይለማርያምን ለማነጋገር ባደረገው ጥረት “በወረዳው በተለያዩ ጊዜ ጥቃቶች እንደሚፈጸሙ” አምነው፤ ነገር ግን ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።     

የኦሮሚያና የአማራ ክልሎችን የሚያዋስነዉ የደራ ወረዳ በተደጋጋሚ ተመሳሳይ ጥቃቶች ይፈጸማል።  ባሳለፍነው ሳምንት በተፈጸመው ጥቃት፤ ከተገደሉት ዘጠኝ ሰዎች መካከል ሽታዬ ዱባለ የምትባል የ 11 አመት ህጻን በጥይት ተመታ መገደሏን እና በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ አይረሳም።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ጂሩ ደዳ በሚባለው ቀበሌ ”ከሃይማኖት ተቋማት ውጭ፤ የመኖሪያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ ከ400 በላይ ከብቶች ተወስደዋል። በርካታ መሰረተ ለማቶች ላይም ውድመት ደርሷል” ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።  

ከዚህ ቀደም ታህሳስ 2015 ዓ/ም የፋኖ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት 18 ሰዎች ሲሞቱ ስድስት ሰዎ ላይ ጉዳት መድረሱን አዲስ ስታንዳርድ ነዋሪዎችን ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወቃል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button