ዕለታዊፍሬዜናህግ እና ፍትህ

እለታዊ ዜና፡ 700ሺህ ዶላር ግምታዊ ዋጋ ያለው ኮኬይን ከአዲስ አበባ ወደ ሆንግ ኮንግ ያስገባ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስራ ዋለ

አዲስ አባባ፣ ጳጉሜ 4/ 2015 ዓ.ም፡- ከአዲስ አበባ ወደ ሆንግ ሆንግ 900 ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ እፅ ይዞ የገባ የ48 ዓመት ግለሰብ በሆንግ ኮንግ ጉምሩክ ተቆጣጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

የሆንግ ኮንግ ጉምሩክ ጳጉሜ 2 ቀን በሆንግ ኮንግ አለም አቀፍ አይር ማረፊያ በቁጥጥር ስር ያዋለው ግለሰብ ሲያዘዋውረው የነበረው አደንዛዥ እፅ 700 ሺህ ዶላር ግምታዊ ዋጋ ያለው መሆኑን የሀገሪቱ መንግስት ዛሬ ባውጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

ምንነቱ ያልገተለፀው ግለሰቡ ከአዲስ አበባ በመነሳት ሆንግ ኮንግ የደረሰው ነሃሴ 30፣ 2015  ሲሆን ከሁለት ቀናት በኋላ ጳጉሜ 2 ቀን አደንዛዥ ዕፁን የያዘበትን ሸንጣ ለመቀበል ወደ ኤርፖርት ባቀናበት ሰዓት በቁጥጥር ስር ውሏል ነው የተባለው፡፡

ጉዳዩ በምርመራ ላይ ነው ያለው የሀገሪቱ መንገስት መግለጫ ግለሰቡ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የ 5 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት እና የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቀዋል ብሏል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button