ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27/ 2016ዐ ዓ/ም፦ ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቶዋን ጋሊንዶ ጋር በቁጥጥር ስር የዋሉት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ በዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ወሰነ። 

የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት “ሁከት እና በጥብጥ በማነሳሳት” ወንጀል ተጠርጥረው ለሁለት ሳምንታት በእስር ላይ የቆዩትን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ፤ ከእስር እንዲለቀቁ የወሰነው በ100 ሺህ ብር ዋስትና ነው።

ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቶዋን ጋሊንዶ ጋር በአዲስ አበባው ስካይ ላይት ሆቴል ቃለ መጠይቅ በማድረግ ላይ እያሉ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ በቴ፤ ገንዘብ በማስያዝ ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ መወሰኑን ጠበቃቸው አቶ ቦና ያዞ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። 

አፍሪካ ኢንተለጀንስ የዜና ወኪል ጋዜጠኛው አንቶዋን ጋሊንዶ እና አቶ በቴ ኡርጌሳ ከአስር ቀን በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው “ ሚስጥራዊ መረጃ አሳልፎ በመስጥት እንዲሁም ከሽኔ እና ከፋኖ ጋር በማሴር ወንጀል” ክስ ቀርቦባቸው ነበር።  

ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ ሃሙስ ከእስር ተለቆ ወደ አገሩ እንዲመለስ የተደረገ ሲሆን አርብ እለት በዋለው ችሎት ላይ አቶ በቴ ፍርስ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የአምስት ምርመራ ቀን ለፖሊስ በመሰጠቱ በዕስር ላይ እንዲቆዩ ተደርጓል። 

በዛሬው ችሎትም ፖሊስ “ምርመራዬን አልጨረስኩም” በሚል ተጨማሪ 11 የምርመራ ቀናትን ጠይቋል።  ጠበቃቸው አቶ ቦና ያዞ ፍርድ ቤቱ አቶ በቴ ኡርጌሳ 100 ሺህ ብር የዋስትና ገንዝብ በማስያዝ ጉዳያቸውን በውጭ እንዲከታተሉ ውስኗል ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button