ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የፕሪቶርያው ስምነት ያስገኘውን ውጤት በማወደስ ሙሉ በሙሉ እንዲተገብ አስር ሀገራት በጋራ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም፡- መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ አስር ሀገራት አውስትራልያ፣ ካናዳ፣ ዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ጃፓን፣ ኔዘርላንድ፣ ኒውዝላንድ፣ ኖርዌ፣ ሲውዲን እና ዩናይትድ ኪንግደም በጋራ ባወጡት መግለጫ የፕሪቶርያው ስምነት ያስገኘውን ውጤት በማወደስ ሙሉ በሙሉ እንዲተገብ ጠይቀዋል።

የፕሪቶርያው ስምምነት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ሰፍኖ የነበረውን ግጭት በማስቀረት፣ የጥይት ድምጽ በማስቆም መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ለማስጀመር መሰረት የጣለው መሆኑን ሀገራቱ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።  የሰፈነውን ሰላም ለማስቀጠል እና ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ በርካታ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ሀገራቱ በመግለጫቸው ትኩረት እንዲሰጥበት ከጠቀሷቸው ነጥቦች መካከል የስምምነቱ አንድ አካል የሆነውን ትጥቅ ማስፈታት፣ ተዋጊዎችን መበተን እና መልሶ ማቋቋም ሂደት፣ ሀገራዊ ምክክር፣ በትግራይ ክልል የሚገኙ ከፌደራል መንግስቱ ውጭ የሆኑ የጸጥታ አካላት ማለትም የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ታጣቂዎች መውጣት፣ የተፈናቃዮች ወደ ቀያቸው መመለስ፣ ሁሉም አገልግሎቶች መጀመር፣ ከጾታዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተጎዱ ዜጎችን ማገዝ፣ ተማኝነት ያለው እና ቅቡል የሆነ የሽግግር ፍትህ ማካሄድ እና የስምምነቱ ትግበራን በትክክል መቆጣጠር ይገኙበታል።

በተቻለ መጠን ሁሉም ስምምነቱን የፈረሙ አካላት ለተግባራዊነቱ እንዲጥሩ እና ለእንቅፋቶቹም በውይይት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ  ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራቱ በመግለጫቸው በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች እየተስፋፉ ያሉት ግጭቶች እንዳሳሰባቸውም አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button