ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና፡ የኢትዮጵያ መንግስት በዘፈቀደ እስር በተቃዋቂዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ከሰሰ 

አዲስ አበባ፣ የካትት 26/2016 ዓ/ም፦ አለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ሂዩማን ራይትስ ዎች የኢትዮጵያ መንግስት ተቃዋሚዎችን፣ ጋዜጠኞችን እና ተቺዎችን በዘፈቀደ በማሰር እና በማቆየት ጥብቅ እርምጃ እየወሰደ ነው ሲል ከሰሰ።  

ሂዩማን ራይትስ ዎች፤ የካቲት ወር ሲቪል በለበሱ የደህንነት ሰዎች የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ዘርፍ ኦፊሰር የሆኑትን በቴ ኡርጌሳ እና ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቶይነ ጋሊንዶ በአዲስ አበባ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉ በቁጥጥር ስር ውለዋል ብሏል

በ24 ሰዓታት በኋላ ፍርድ ቤት የተወሰዱ መሆኑን የገለጸው ሂዩማን ራይትስ ዎች ችሎቱ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፍቅዷል ብሏል። የአልም አቀፍ ተጽዕኖን ተከትሎ ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቶይነ ጋሊንዶ ከእስር ተለቆ ወደ ሀገሩ ፈረንሳይ መደረጉን ድርጅቱ አስታውቋል።

ነገር ግን በቴ ኡርጌሳ እስር እንዲራዘመ ተደርጓል ያለው የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አርብ የካቲት 22 ቀን ዓቃቢ ህግ ከኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አማጺ ቡድን ጋር ግንኙነት አለው በሚል ምርመራ እየተደረገበት ነው ማለቱን ገልጿል። ችሎቱ በቴ እስከ የካቲት 27 በዕስር ላይ እንዲቆይ አዟል ብሏል። 

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ከበቴ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት በቅርቡ ቢያንስ ሌሎች አምስት የተቃዋሚ ፖለቲከኞችን በቁጥጥር ስር አውለዋል ሲል ገልጾ በእስር ላይ ከሚገኙት ውስጥ፤ መንግስት በአማራ ክልል እያከናወነ ያለውን ድርጊት የሚተቹት እና የፓርላማ አባል የሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ደሳለኝ ጫኔ ይገኙበታል ብሏል።

“እነዚህ እስሮች አሁን ላይ በኢትዮጵያ ውስጥ ማንም ሰው በዘፈቀደ ከመታሰርና ከመቆየት ደህንነቱ የተጠበቀ አለመሆኑን ያሳያል” ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ገልጿል። “የኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ አጋሮች፤ ያለአግባብ የሚደረጉትን የእስራት ማውገዝ እና መንግስት በሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ ያለው አለምቻል መቃወም አለባቸው” ብሏል

በቅርቡ ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመው በአማራ ክልል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር ተያይዞ በረካታ ሰዎች ታስረዋል። የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ ቢያንስ  ስምንት ጋዜጠኞች መታሰራቸውን ማስታወቁ ይታወቃል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button