ዕለታዊፍሬዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዕለታዊ ዜና፡ የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9/ 2016 ዓ/ም፡– የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች የትምህርት ማስረጃ እየተጣራ መሆኑን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አስታወቀ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኮሚሽኑን የስድስት ወራት አፈፃፀም ሰሞኑን ገምግሟል።

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራው ከታሰበው በላይ ቁጥሩ የሰፋ እና ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ የሚገኝ ነው።

ለትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሂደቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሰብሳቢነት የሚሳተፍበትና የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ የትምህርትና ሥልጠና እና የትምህርት ሚኒስቴር የተካተቱበት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ እየተሠራ የሚገኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ዲግሪና ከዲግሪ በላይ የትምህርት ማስረጃ ያላቸው የ51 ሺህ የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ እንደሚገኝ ኮሚሽነር ኃይሌ (ዶ/ር) አስታውቀው፤ ከዲግሪ በታች የትምህርት ዝግጅት ያላቸው ሠራተኞች ማስረጃ የማረጋገጡ ሥራ በቀጣይ የትግበራ አካል እንደሚሆን ጠቁመዋል ሲል ኢፕድ ዘግቧል።

ሥራው በአምስት ምዕራፍ ተከፍሎ እየተሠራ ይገኛል ያሉት ኮሚሽነር መኩሪያ (ዶ/ር) የፌዴራል ተቋማትን፣ የሚኒስትሮችና የተጠሪ ተቋማትን ማስረጃ ማጥራት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሆኖ ቢሠራ የተሻለ እንደሚሆን በማመን ቅድሚያ ተሰጥቶት እየተሠራ ነው ብለዋል።

ሦስቱ ምዕራፎች ሲጠናቀቁ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማስረጃ ማጣራት ይከናወናል። በተለይም ኮሚቴው የመንግሥት ከፍተኛ ተቋማት ማስረጃ ማጥራት እቅድ አውጥቶ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

እንደርሳቸው ማብራሪያ፤ በሁለተኛ ምዕራፍ የመጨረሻው ደረጃ ሥራ ወደ መገባደዱ ሲጠጋ የሕግ አውጭ፣ ተርጓሚ አካልና የዴሞክራሲ ተቋማት መረጃ ተሰብስቦ እየተጣራ ነው። በመቀጠልም በሶስተኛ ምዕራፍ የክልል መንግሥታት የትምህርት ማስረጃ የማጥራት ሥራ ለመተግበር በእቅድ ተይዟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button