ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የአማራ ክልል አስከርካሪዎች በነዳጅ እጥረት እና በዋጋ ንረት ምክንያት መቸገራቸውን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ያሉ አሽከርካሪዎች በተከሰተው ከፍተኛ የነዳጅ እጥረት እና በዋጋ ንረት ምክንያት መቸገራቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ። አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች ከላፈው ሳምንት ጀመሮ በክልሉ አንዳንድ ከተሞች የተከሰተው የነዳጅ እጥረት አንቅስቃሴዎቻቸን ማደናቀፉን ገልጸዋል።

በአማራ ክልል መዲና ባህር ዳር የሚገኝ አንድ አሽከርካሪ፤ “የነዳጅ አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ምክንያት በየዕለቱ ጠዋት ላይ ነዳጅ ለመግዛት የሚሰለፉ ሾፌሮች ነዳጅ ሳያገኙ ይመለሳሉ። ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች በስራ ላይ አይደሉም ማለት ይቻላል” ብሏል። 

በባህር ዳር የሚገኝ ሌላ የታክሲ ሾፌር እንደገለጸው፤ የከባድ ጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የነዳጅ አቅርቦት ውስን በመሆኑ ምክንያት ነዳጅ ለመሙላት ሌሊቱን እንዲሁም ብዙ ቀናትን ለመጠበቅ ተገደዋል ሲል ገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም፤ ታክሲ ሾፌሮች በጥቁር ገበያ በፍተኛ ዋጋ የሚሸጥ ነዳጅን መግዛት ግድ ሆኖባቸዋል ብሏል።    

ባሳለፍነው ሳምንት ዶቸ ቨይለ በባህር ዳር የነዳጅ እጥረት መከሰቱን የጥቁር ገበያ መስፋፋቱን ዘግቧል።  ለዜና አውታሩ አስተያት የሰጠ አንድ የባርዳር ከተማ አሽከርካሪ፤ “በጥቁር ገበያው 2 ሊትር ቤንዚን ከ350 ብር በላይ ይሸጣል፣ 77 ብር በሊትር መሸጥ የነበረበት ነው ወደ 175 ብር በሊትር እየተሸጠ ያለው፣ አንዱ ሊትር 175 ብር ከተሸጠ 90 ብር ያክል በአንድ ሊትር በህገወጥ መንገድ ጭማሪ ተደርጎበታል ማለት ነው” ሲል ገልጿል።

“ከአንድ ቦቴ ነዳጅ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር በህገወጥነት መንገድ ሸጦ ትርፍ ያገኛል” የሚለው አሽከርካሪው ቁጥጥርና ክትትል ባለመኖሩ፤ ለዚህ የክልሉ ባለስልጣናትን ተጠያቂ አድርጓል።

የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢብራሂም መሐመድ ለዲቸ ቨለ እንደገለጹት፤ የነዳጅ ስርጭት ላይ ችግር ገጥሟቸዋል።  በክሉሉ ያለው “የፀጥታ ችግር” ምክንያት የነዳጅ አቅራቢዎች እንቅስቃሴ መገደቡን ገልጸዋል። ነገር ግን ችግሮችን ለማስተካከልና ያለውን የነዳጅ እጥረት ለመከላከል አሠራር መዘርጋቱን ተናግረዋል። 

ኃላፊው፤ አማራ ክልል ከ280 በላይ የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች እንደሚገኙ ገልጸው 253ቱ በስራ ላይ እንደሆኑም አስረድተዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ነገር ግን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገረው አሽከርካሪ የነዳግ ማደያዎች ሆን ብለው የነዳጅ አቀረቦትን እየገደቡ ነው ሲል ወቅሷል። 

የዋጋ ጭማሪው የታክሲ ሾፌሮች ሥራቸውን እንዳይሰሩ ፈተና እየፈጠረባቸው ነው የሚለው አሽከርካሪው፤ በዚሁ ምክንያት “በአጭር ርቀት 5 ብር የነበረው ታሪፍ ወደ 10 ብር ከፍ ብሏል” ሲሉ አሽከርካሪው ተናግረዋል። 

በደብረ ብርሃን በታክሲ ስራ ላይ የተሰማራ አስከርካሪ፤ “በከተማው ውስጥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የነዳጅ እጥረት አለ” ሲል ገልጿል።  አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button