ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት በአደባባይ፣ ህዝብ በተሰበሰበበት እንዲከበሩ ተፈቀደ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14/2016 .ም፡ በአማራ ክልል መስከረም 16 እና 17 2016 ዓ.ም የሚከበሩትን የመውሊድ፣ የደመራና የመስቀል በዓላት የሃይማኖቶቹ ሥርዓት በሚፈቅዱት መንገድ እንዲከበሩ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ከአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ አስታወቀ። በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ የህዝብ ስብሰባዎች መከልከላቸውን ያወሳው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መምሪያ ዕዙ መግለጫ ነገር ግን እነዚህ በአላት ሀይማኖታዊ የአደባባይ በአላት በመሆናቸው እንዲካሄዱ መፈቀዱን አስታውቋል።

በክልሉ የሕዝብ ስብሰባዎች በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ የተከለከሉት ጽንፈኛና ዘራፊ ኃይሎች በሕዝብ ላይ ሊያደርሱት የሚችሉትን ጉዳት ለመቀነስ ታስቦ የተደረገ ነው ያለው መግለጫው መስከረም 16 እና 17 የሚከበሩት ሃይማኖታዊ በዓላት የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው ለበዓላቱ ሥነ ሥርዓት ሲባል የአደባባይ መሰባሰብን መፍቀድ ማስፈለጉን አመላክቷል።

የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ መምሪያ ዕዝ በመግለጫው ባስተላለፈው ሶስት ትዕዛዛት ታጅቦ በአላቱ እንደሚከበሩ ጠቁሟል። የተላለፉት ትእዛዛትም አንደኛ በክልሉ ህዝቡ የሚሰበሰበው ለሃይማኖታዊ የበዓል አከባበር ሥነ ሥርዓት ብቻ  የሚውሉ መሆናቸውን፣ ሁለተኛ ህዝቡ እንዲሰባሰብ የተፈቀደለት የበዓላቱ አከባበር ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ብቻ መሆኑን እና በእነዚህ አከባበሮች ወቅት ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል ከጸጥታ አካላት ጋር መተባበር ግዴታ ነው የሚሉት ይገኙበታል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button