ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ አሜሪካ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብና በሰሜን ሸዋ ዞን የተፈፀሙ ጥቃቶች እንዳሳሰባት ገለጸች 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17/2016 ዓ/ም፡_ አሜሪካ በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ሸዋ ዞን በተፈጸሙ ጥቃቶች፤ ሲቪሎች መገደላቸው፣ ጉዳት መደረሱ እና የሰዎች መፈናቃል እንዳሳሰባት ገለጸች።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ፤ “የትኛውም የግጭት ተዋናይ ሁከትን በመጠቀም ሰዎችን ከቤታቸው ማፈናቀል የለበትም”  ሲሉ አሳስቧል። 

አምባሳደሩ ዛሬ መጋቢት 17 ቀን ባስተላለፉት መልዕክት አገራቸው አሜሪካ፤ የኢትዮጵያ ውስብስብ የፖለቲካ እና የፀጥታ ቀውሶችን ለመፍታት የሲቪሎችን ጥበቃ እና የውይይት ቁርጠኝነት እንዲኖር ጥሪ ማቅረቧን ገልጸዋል። 

በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጂሌ ጥሙጋ ወረዳ “በፋኖ ታጣቂዎች እና የክልሉን ፖሊስ ደምብ ልብስ በለበሱ ኃይሎች” ከየካቲት 30፣ 2016 ዓ/ም ጀምሮ በተፈጸመ “የተቀናጀ ጥቃት” በርካታ ሰዎች መሞታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ነዋሪዎችን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። 

በጥቃቱ 27 የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን እና ከ40 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል።  በጂሌ ጥሙጋ ወረዳ በሚገኙ ከ20 በላይ ቀበሌዎች ግጭት መፈጸማቸውን አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል። 

በተመሳሳይ በክልሉ ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ መጋቢት 12 ቀን በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ስምንት ሰዎች ሲሞቱ ከ20 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። 

የአጣዬ ተከማ ነዋሪ በከተማዋ የተፈጸመው ጥቃት አስመልክቶ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለጸው፤ የስምንት ሰዎች ህይወት ባለፈበት ጥቃት፤ የ“ሸኔ” ታጣቂዎች ሲል የገለጻቸውን አካላት ተጥያቂ አድርጓል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሌላኛው የከተማው ነዋሪ ደግሞ ጥቃቱን የፈጸሙት የፋኖ ታጣቂዎች ናቸው ሲል ገልጿል።  በሰንበቴ ከተማ የህክምና ባለሙያ ለአዲስ ስታንዳርድ በጥቃቱ ጉዳት የደረሰብናቸው ሰዎች በሰንበቴ ከተማ እና በአዳማ  ህክምና እየተከታተሉ ነው ስትል ገልጻለች። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button