ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የክልል የፍትሕ ተቋማት የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ በቂ ትብብር እንደማያደርጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/ 2016 ዓ/ም፦ የክልል የፍትሕ ተቋማት ችግር የተገኘባቸውን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያስችል በቂ ትብብር እንደማያደርጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም አስታወቀ።

በተለይም የ #ባህርዳር ከተማ አስተዳደር፣ በ #ሀዋሳ ከተማ አስተዳደርና የ #ወራቤ ከተማ አስተዳደር ላይ ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ላይ አቤቱታ ቀርቦ እንባ ጠባቂ ጉዳዩን መርምሮ የሚሰጠውን ማስተካከያ ከመተግበር አኳያ ሰፊ ችግር ታይቷል ሲሉ በኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የይግባኝና የውሳኔ ማስፈጸም መሪ ሥራ አስፈጻሚ ደነቀ ሻንቆ ገልጸዋል። 

በዚህም ጉዳዩን ወደ ሕግ ለማቅረብ እንቅስቃሴዎች ሲጀመሩ የከተማዎቹ ፍትሕ አካላት አስፈጻሚውን ለመጠየቅ የሚያደርጉት ትብብር እጅግ አነስተኛ ሆኗል ሲሉ አቶ ደነቀ ለኢፕድ ተናግረዋል።

ችግሩ በተጠቀሱት ከተማዎች ላይ የጎላ ቢሆንም በተለያዩ የክልል አካባቢዎች የሚገኙ የፍትሕ አካላት ተጠያቂነትን ለማስፈን በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያላቸው ትብብር አነስተኛ መሆኑን አንስተዋል።

የፍትሕ አካላት ከዴሞክራሲ ተቋማት ጋር በይበልጥ በትብብር መሥራት እንዳለባቸው ጠቁመው፤ እንባ ጠባቂም ከፍትሕ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት ማካሄዱን አመላክተዋል።

ወደ ተቋሙ የሚመጡና እልባት የማያገኙ አብዛኛዎቹ ጉዳዮች ስልጣንን ያለአግባብ በመጠቀም የሚፈጸሙ ጥፋቶች ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ጠቁመው፤ ወደ ፍርድ ቤትና በልዩ ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቡ መዝገቦች መኖራቸውን መሪ ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት ላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ለመመርመር በሚደረግ ጥረት በቂ መረጃ ያለማቅረብና ጉዳዩን መርምሮ የሚሰጠውን ማስተካከያ ተግባራዊ ያለማድረግ ችግር መኖሩንም አስታውቀዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button