ዜናፖለቲካህግ እና ፍትህ

ዜና፡ አቶ ክርስቲያን ተደለ እና ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14 የሽብር ተከሳሽ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 28/ 2016 ዓ/ም፡_ የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ካሰራቸዉና ከከሰሳቸዉ 52 ተጠርጣሪዎች መካከል፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ክርስቲያን ታደለና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል ዮሐንስ ቧያለዉን ጨምሮ 14ቱ ትላንት መጋቢት 27፣ 2016 ለሁለተኛ ጊዜ በፌዳራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ፍርድ ቤት የቀረቡት የእምነት ክሕደት ቃላቸዉን ለመስጠት የነበረ ቢሆንም፤ በደል ደርሶብናል በማለታቸዉ ችሎቱ ተከሳሾች ያቀረቡትን አቤቱታ ሲያደምጥ መዋሉን ዶቸ ቬለ ዘግቧል። 

ከተከሳሽ ጠበቆች  የክስ ንባቡ “ሥነ ሥርዓታዊ” ቢሆንም “አፋጣኝ የሆኑ የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ ከተከሳሾች በጋራ የሚቀርቡ ጥያቄዎች ስላሉ” ችሎቱ የክስ ማንበቡን ጉዳይ ትቶ የተከሳሾችን አቤቱታ እንዲያደምጥ ጥያቄ ቀርቧል ብለዋል።

አቤቱታውን የተቀበለው ችሎቱ በስፍራው ለዘገባ የታደሙ ጋዜጠኞች እና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ተወካይ “ለችሎቱ ፈቃድ አልጠየቃችሁም” በሚል  ችሎቱን መታደም እንጂ መዘገብ እንደማይችሉ ተነግሯቸው ከችሎቱ መውጣታቸውን ዘገባው አመላክቷል።

ጠበቆች የተከሳሾችን የመብት ጥሰት አቤቱታ መገናኛ ብዙኃን ሊዘግቡት እንደሚገባ እና እንዲህ ያለ ክልከላ ገጥሞ እንደማያውቅ ጠቅሰው ቢከራከሩም፣ ችሎቱ ከመገናኛ ብዙኃን ዘገባን የተመለከተ ጥያቄ አልቀረበም በሚል ጥያቄ እስካልቀረበ ድረስ ጋዜጠኞች ችሎቱን እንዳይዘግቡ ጥብቅ ትእዛዝ አስተላልፏል ተብሏል።

የችሎቱን ሂደት በተመለከተ የተከሳሾች ጠበቃ የሆኑት አቶ ሰለሞን ገዛኸኝን፤ አቶ ክርስትያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለዉ ደረሰብን ያሉትን የመብት ጥሰት ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ብለዋል።

አቶ ዮሐንስ ቧያለዉ፤ “የጸጥታ ሓይሎች ጥቃቶች እያደረሱባቸው እንደሆነ እንዲሁም ማንነትን መሠረት ላደረገ ጥቃት፤ ለህመም መጋለጣቸውን” ገልጸዋል ተብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

አቶ ክርስትያን ታደለም በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት፤ “ወርቅ የአንገት ሃብል፣ ሁለት የጣት ቀለበት እንደተወሰደባቸው” ትላንት በዋለው ችሎት ላይ ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል ሲሉ አቶ ሰለሞን ገዛኸኝን አስረድተዋል።  በተጨማሪም የሞባየላቸውን ቁልፍ እንዲከፍቱ “በሽጉጥ እንዳስፈሯሯቸው እና ጣታቸውን እንደተመቱ” አክለው አስረደተዋል ትብሏል።

ተከሳሾቹ  ከሳምንት በፊት እሥር ቤት ውስጥ ሆነው በፃፉት ደብዳቤ “ማንነትን መሠረት ያደረገ ስድብ፣ ዘለፋ ፣ ማስፈራራት፣ ዛቻ ፣ ድብደባ እና ዝርፊያ” እንደተፈፀመባቸው ገልፀው ነበር።

ፍርድ ቤቱ ተፈጸሟል ስለተባለው የመብት ጥሰት እና የሌሎችንም ለመስማት ለቀጣይ ማክሰኞ ሚያዚያ 1 2016 ቀጥሮ መሰጠቱን ጠበቃው አክለው ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል የሆኑት 1ኛ ተከሳሽ አቶ ዮሃንስ ቧያሌው በሆኑበት በዚህ የክስ መዝገብ ሥር፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ክርስትያን ታደለ፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት አባል የሆኑት ዶክተር ካሳ ተሻገር፣ አቶ እስክንድር ነጋ ፣ አቶ ዘመነ ካሴ እና ዶክተር ጫኔ ከበደ ይገኙበታል። 

ለተከሳሾች እና ጠበቆቻቸው የደረሰው የክስ ዝርዝር ተከሳሾች “የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማ ለማስፈፀም” ተሰባስበው መምራት የሚል ክስ ነው። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button