ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ እያካሄደች መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27/2016 ዓ.ም፡- የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከ2 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋ ያለው ኢንቨስትመንት በኢትዮጵያ እያካሄደች መሆኑን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዑመር ሁሴን አስታወቁ።

ሁለቱ ሀገራት በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊና ቱሪዝም ዘርፎች ጠንካራና እያደገ የመጣ ግንኙነት አላቸው ሲሉ አምባሳደሩ መግለጻቸውን ያስታወቀው ኢፕድ ዘገባ ኢትዮጵያውያን በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ብዙ ኢንቨስትመንቶች አላቸው ማለታቸውንም ጠቁሟል።

በትራንስፖርት፣ ኢንቨስትመንትና የሰራተኞች ማሻሻያን የሚመለከቱ ስምምነቶች መኖራቸውን የጠቆሙት አምባሳደሩ ስምምነቶች ተግባራዊ እየተደረጉ በመሆኑ ለኢኮኖሚውና ለማህበራዊ መሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል በቅርብ እያደገ የመጣው የትምህርት ዘርፍ ሌላው የግንኙነት ማሳያ ነው ያሉት አምባሳደሩ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በብዛት የሳይንስ ትምህርቶችን በነጻ ይማራሉ፣ በዚህ አመት ብቻ ከ250 በላይ ተማሪዎች እድል አግኝተዋል ብለዋል።

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ያሉ ኢትዮጵያውያን የተደራጁና ሀገርን የሚደግፉ ናቸው ያሉት አምባሳደር ዑመር፣ በኤምባሲው አስተባባሪነት ለሀገራዊ ፕሮጀክቶች በዓመት እስከ ግማሽ ሚሊዮን ዶላር መዋጮ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button