ዜናህግ እና ፍትህ

ዜና: ኤርትራ በእስር ላይ የነበሩ 46 የትግራይ እስረኞችን ለቀቀች፤ ከፊሎች ከአንድ አመት በላይ በእስር ላይ የቆዩ ናቸው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 5/2016 ዓ/ም፦ ኤርትራ ከሁለት ወር እስከ ከአንድ አመት በላይ በእስር ላይ ያቆየቻቸውን 46 የትግራይ እስረኞችን በትላንትናው ዕለት መልቀቋ ተገለጸ። 

አስረኞቹ መለቀቃቸውን ያረጋገጡልን ምንጭ እንደገለጹት፤ አብዛኞቹ አስረኞች የተወሰዱት ከትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ ዞን ታህታይ አዲያቦ ወረዳ ነው።

የወረዳው የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ መብራህቶም ገዛኢ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ግለሰቦቹ በባሬንቱ እስር ቤት ውስጥ እንደታሰሩ ገልጸዋል። ይህ እስር ቤት የሚገኘው በኤርትራ አስተዳደራዊ ክልል ጋሽ-ባርካ ውስጥ ነው።

መብራህቶም በትላንትናው እለት የተፈቱት እስረኞች ወደ ኤርትራ ተወስደው ከመታሰራቸው በፊት ታግተው እንደነበር አብራርተዋል።

የታህታይ አዲያቦ ወረዳ በሰሜን በኩል ከኤርትራ ጋር ድንበር ይጋራል።

በህዳር 2022 በፕሪቶሪያ ዘላቂ ጦርነት ማቆም ስምምነት ቢፈረምም፤ በትግራይ ውስጥ በኤርትራ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች  በሚገኙ ግለሰቦች ላይ የሚፈጸመው እገታ ተባብሶ መቀጠሉን መረጃዎች ያመለክታሉ።

እኤአ ታህሳስ ወር 2023 አዲስ ስታንዳርድ በምስራቅ ትግራይ ዞን ጉሎመቅዳ ወረዳ 26 ግለሰቦች በኤርትራ ሃይሎች መታገታቸውን ዘግቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የትግራይ ጦርነትን ትከትሎ የዛላምበሳ ከተማ እና የጉሎምቀዳ ወረዳ ስር የሚገኙ ስድስት ቀበሌዎች በብዛት በኤርትራ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆናቸውን የክልሉ ባለስልጣናት ጠቁመዋል።

መስከረም ወር የኢሮብ ወረዳ ባለስልጣናት በአስር ወራት ውስጥ 28 ወጣቶች በኤርትራ ኃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ገልጸዋል።

ድርጊቱን ተከትሎ የኢሮብ ወረዳ አስተዳደር ኃላፊ የሆኑት አቶ እያሱ ምስጊና እንደተናገሩት፤ የታጋቾቹ ቤተሰቦች ግለሰቦቹ የት እንዳሉ አያውቁም ብለዋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button