ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የ680 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 23/2016 ዓ.ም፡- በትግራይ ተካሂዶ በነበረው ጦርነት ሳቢያ ተቋርጦ የነበረው የአውሮፓ ህብረት ድጋፍ እንደሚቀጥል የህብረቱ የአለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ዩታ ኡርፒላይነን አስታወቁ። ህብረቱ ለኢትዮጵያ የ680 ሚሊየን ዶላር የእርዳታ ድጋፍ እንደሚሰጥ ይፋ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሰላም፣ የሽግግር ፍትህ እና ሪፎርም ለማምጣት እየጣረች ትገኛለች፣ ህብረቱ ይህንን ሂደት ሳያለሳልስ እየደገፈ ይገኛል ሲሉ ኮሚሽነሯ ተናግረዋል። የአውሮፓ ህብረት እና ኢትዮጵያ ግንኙነታቸውን በተደራጀ ፖለቲካዊ ውይይት እና አጋርነታቸውን በማጠናከር ለማደስ እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ህብረቱ ለኢትዮጵያ መስጠት ያቋረጠውን ቀጥተኛ የበጀት ድጋፍ ለመቀጠል ግን የኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያሟላቸው የሚጠበቁ ጉዳዮች እንዳሉ ኮሚሽነሯ ጠቁመዋል። የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ያቀረበውን የሪፎርም ፕሮግራም ላይ ስምምነት መድረስ እና የፖለቲካ መስተካከሎች ኢትዮጵያ እንድታሟላቸው ከተጠየቀችባቸው መስፈርቶች መካከል መሆናቸውን አመላክተዋል።

ህብረቱ ለኢትዮጵያ የሰጠው ድጋፍ ከሶስት አመታት በኋላ የመጀመሪያ መሆኑም ተጠቁሟል። የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሰጠው ድጋፍ ይፋ የሆነው የህብረቱ የአለም አቀፍ አጋርነት ኮሚሽነር ዩታ ኡርፒላይነን ከገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽኔ ጋር በጋራ በአዲስ አበባ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ነው።

የህብረቱ ድጋፍ ኢትዮጵያ ከጦርነቱ ማግስት ለምታደርገው መልሶ ግንባታ እና እያካሄደችው ላለው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button