ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከ100 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3/2016 ዓ/ም፦ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከ100 ሺህ በላይ የቀድሞ ተዋጊዎችን በሁለት ዙር ትጥቅ ማስፈታቱን አስታወቀ።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ረዳኢ ሃልፎም ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ፤ ሂደቱ ህዳር 2022 በፕሪቶሪያ በተደረሰው ዘላቂ ግጭት የማቆም ስምምነት ድንጋጌ መሰረት መከናወኑን ገልጸዋል። 

በመጀመሪያ ዙር ትጥቅ የማስፈታት ሂደት ከ 50 ሺህ በላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ተዋጊዎች ጥቅት እንዲፈቱ ተደርጓል። 

የመጀመሪያ ዙር ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት ሂደት በተመለከተ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝዳንት ጄኔራል ታደሰ ወርደ፤ ኀምሌ 2015 በሰጡት መግለጫ፤ የቀድሞ ተዋጊዎችን የማስፈታት ስራው በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ብቻ መከናወኑን ገልፀዋል ።

ራዳኢ በቅርቡ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ባደረጉት ቆይታ ሁለተኛው ዙር ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታቱ ስራ ያለ ብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽነርን ኮሚሽን ድጋፍ እና ተሳትፎ በክልሉ በቻ መከናወኑን ተናግረዋል። 

“ከ100 ሺህ በላይ ተዋጊዎቹን ትጥቅ የማስፈታቱ ስራ የተከናወነው የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ ትግበራ ከመጠበቅ፤ ተዋጊዎቹን  ለመበተን እና መልሶ ለማቋቋም የሚሆን በቂ አቅርቦት በሌለብት ነው” ሲሉ የገለጹት ኃላፊው፤  “ይህ የሚያሳየው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የፕሪቶሪያ ስምምነትን ለመተግበር ያለውን ቁርጠኝነት ነው” ብለዋል።

በፕሪቶሪያው ስምምነት መሰረት የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታትና መልሶ የሟቋቋም ስራን የማቆጣጠር ኃላፊነት የተሰጠው እና ታህሳስ 2015 የተቋቋመው ብሔራዊ ተሀድሶ ኮሚሽን፤ በስምንት ክልሎች 371 ሺህ 971 የቀድሞ ተዋጊዎች መኖራቸውን እና 75 በመቶ ወይም 274 ሺህ የሚሆኑት የሚገኙት በትግራይ ክልል የሚገኙ መሆኑን አስታውቋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ፤ እነዚህ ትጥቅ የፈቱት ሰዎች፤ የመኖሪያ ቤት እጥረት፣ የስራ እድል ማጣት እና መሰረታዊ ፍላጎቶችን የማግኘት ችግር እንዳጋጠማቸው አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።  “”በከባድ የኢኮኖሚ ችግር እና የስራ እድል እጦት እየተጋፈጡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ” ብለዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button