ዜናፖለቲካ

ዜና፡ አሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ የአፍሪካ ልማት ባንክ ሠራተኞች ላይ ድብደባ ያደረሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠየቁ

አዲስ አባባ፣ ታህሳስ 18/ 2016 ዓ/ም፡ በቅርቡ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ልማት ባንክ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አብዱል ካማራን ጨምሮ ሁለት የባንኩ ሠራተኞች ላይ ድብደባ ያደረሱ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ የአሜሪካ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ካናዳ መንግስት ጠየቁ። 

ሀገራቱ ኢትዮጵያ ባለው ኢምባሲዎቻቸው በኩል ባወጡት መግለጫ በቬይና ኮንቬንሽ የተደነገጉ መብቶችን መጠበቅ እና ማክበር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።

ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዲፕሎማቶች ያለስጋት ስራቸውን እንዲያከናውኑ የቬይና ስምምነት እንዲጠበቅ እና በሰራተኞቹ ላይ የተፈጸመው አካላዊ ድብደባ እና እስር ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርባለች።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ መንግስት በባንኩ ሰራተኞች ላይ የተፈጸመው “ድብደባ እና እስር” እንዳሳሰበው በመግለጽ በቬይና ኮንቬንሽ የተደነገጉ የዲፕሎማቲክ መብቶችን ያላከበሩ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ሲል አሳስቧል።  

በተመሳሳይ መልኩ ጥቃት አድራሾቹ “ተጠያቂ ባለመደረጋቸው” የተሰማውን ቅሬታ ያልሸሸገው የካናዳ መንግስት ባንኩ የውጭ ዜጎችን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት መወሰኑ እንዳሳሰበው አክሎ ገልጿል።

የአፍሪካ ለማት ባንክ በቀረቡ ባወጣው መግለጫ ሁለት ሠራተኞቹ “በመንግስት ጸጥታ ሀይሎች ድብደባ እና እስር” እንደደረሰባቸው መግለጹ ይታወቃል። ይህን ተከትሎም ባንኩ ከሳምንት በኋላ ባወጣው መግለጫ ሁሉንም አለም አቀፍ  ሰራተኞቹ በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ ሊያሰወጣ መሆኑን አስታውቋል።

ባንኩ እዚህ ወሳኔ ላይ የደረሰው “የኢትዮጵያ መንግስት በሰራተኞቹ ላይ ድርጊቱን የፈጸሙ አካላት ላይ ምርመራ አድርጎ እንዲያሳውቀው ጠየቆ ተፈጻሚ ባለማደረጉ ነው” ሲል አሳውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ደይሊ ኔሽን የዜና ወኪል በሰራተኞቹ ላይ ድብደባና እስር የፈጸሙት የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚንስትር ጠባቂዎች መኾናቸውን ሰምቻለሁ ሲል ዘግቧል። “መንግሥት ለባንኩ መክፈል ያለበት 5.2 ሚሊዮን ዶላር ዓመታዊ መዋጮ ለባንኩ እንዳልደረሰ የባንኩ ሃላፊዎች መግለጣቸው ድብደባው ለመፈጸሙ መክንያት” እንደሆነ ዘገባው ጠቅሷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button