ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በአማራ ክልል በሚገኝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መጠለያ ካምፕ ላይ ጥቃት ተፈጸመ፤ የሱዳን ስደተኞች ለቀው ለመውጣት ተገደዋል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 26/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል በሚገኝ ኩመር ተብሎ በሚጠራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መጠለያ ካምፕ ላይ ታጣቂዎች ባደረሱት ተከታታይ ጥቃት የሱዳን ስደተኞች ለቀው ለመውጣት መገደዳቸው ተጠቆመ።

በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች በመጠለያ ካምፑ ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እንደሚያደርሱ፣ ዘረፋ እንደሚፈጽሙ ከመንግስታቱ ድርጅት እና ከሶስት ስደተኞች ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

ኩመር ተብሎ በሚጠራው መጠለያ ካምፕ ውስጥ ከሰባት እስከ ስምንት ሺ ሱዳናውያን ስደተኞች ተጠልለው እንደሚገኙ የጠቆመው ዘገባው አብዘሃኛዎቹ በጥቃቱ ሳቢያ ካምፑን ጥለው በመውጣት በእርግራቸው ለመጓዝ መገደዳቸውን አስታውቋል።

ፖሊስ መጠለያ ካምፑን ጥለው የወጡ ስደተኞቹን ማስቆሙን የጠቆመው ሮይተርስ የዜና ወኪል ካምፑ ከሱዳን ድንበር በ70 ኪሎሜትር ርቀት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በመጠለያው ከነበሩ ስተኞች መካከል አንድ ሺ የሚጠጉ ስደተኞች መጠለያ ካምፑን ጥለው ረቡዕ ሚያዚያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም መውጣታቸውን አመላክቷል ያለው ዘገባው በተከታታይ የሚደርስባቸው ጥቃት አና የጸጥታ ቸግር ዋነኛ መንስኤው መሆኑን ገልጿል ብሏል።

የፌደራል መንግስቱም ይሁን የክልሉ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጡት ያደረገው ሙከራ እዳልተሳካለት ሮይተርስ አስታውቋል።

በኩመር መጠለያ ካምፕ ውስጥ ተጠልለው የሚገኙ ሱዳናውያን ስደተኞች ለመንግስታቱ ድርጅት የሰደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በቅርቡ በጻፉት ደብዳቤ ለተከታታይ ወራት በመጠለያው ካምፕ ላይ ጥቃት መፈጸሙን እና ስጋት ማየሉን እደሳታወቁ የዜና አውታሩ በዘገባው አካቷል። እየደረሰባቸው ካለው ጥቃቶች ውስጥ በመጠለያው ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን በማገተ ማስለቀቂያ ገንዘብ እንደሚጠይቁ፣ በመሳሪያ የተደረገፈ ዘረፋ እንደሚፈጸምባቸው እና ግደያዎቸ መኖራቸውን ተጠቅሰዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“ወደ እዚህ መጠለያ ከመጣንበት ያለፈው አመት ሰኔ ወር ጀምሮ ተደጋጋሚ ጥቃት ይፈጸምብናል፣ እንታገታለን፣ እንገደላለን፣ ከአሁን በኋላ እዚህ መቆየት አንችልም፤ ጦርነት ቢኖርም ወደ ሀገራችን እንመለሳለን” ሲል አንድ ስደተኛ በስልክ እንደነገረው ሮይተርስ በዘገባው አካቷል።

የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ጽ/ቤት በበኩሉ ለዜና አውታሩ በደብዳቤ በሰጠው ምላሽ በካምፑ ያለው ሁኔታ እጅግ አስቸጋሪ ነው ሲል በመግለጽ ስደተኞች መጠለያውን ጥለው እየወጡ ያሉት ስጋት ስለአደረባቸው ነው፤ ወንጀል፣ ንጥቂያ፣ በመሳሪያ የተደገፈ ዝርፊያ፣ ግድያ እና እገታ መፈጸሙን ተከትሎ ነው ሲል ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button