ዜናፖለቲካ

ኢዜማ ሊቀመንበሩ ዶ/ር ጫኔ ከበደ መታሰራቸውን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 14/2016 .ም፡ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ጫኔ ከበደ ትላንት መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፀጥታ አካላት እንደታሰሩበት አስታውቋል።

የፓርቲቅ ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት መስከረም 14 ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተል ኮሚቴ ማቋቋሙን የጠቆመው መግለጫው እያንዳንዱን ሂደትም እየተከታተለ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል፡፡

ዶ/ር ጫኔ ከበደ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ታርጋ በሌለው መኪና እና ምንም ዓይነት የእሥር ማዘዣ ወረቀት ባልቀረበበት ሁኔታ መሆኑን ያስታወቀው ፓርቲው በምን ምክንያት እንደተያዙም የተገለጸ ነገር አለመኖሩን ዛሬ መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።  

ይህን መሰል ህግ እና ሥርዓት ያልተከተለ እርምጃም በፅኑ የምናወግዘው መሆኑን እናሳውቃለን ያለው የኢዜማ መግለጫ ፓርቲው ጉዳዩን በጥንቃቄ እና በቅርበት እየተከታተለው እንደሚገኝ ለአባላት እና ደጋፊዎች አሳውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button