ፖለቲካ

ዜና: እያንዳንዱ ድሮን ታጥቆ የሚሰማራው ሚሳኤሎች ዋጋ 3.5 ሚሊዮን ብር እንደሚገመት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም፡- በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ሆሮ ጉዱሩ ውስጥ የእርሻ ማሳ ላይ ወድቋል የተባለ ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) ተንቀሳቃሽ ምሥል እና ፎቶ በስፋት ሲሠራጭ ነበር።

የወደቀው ድሮን ባይራክተር ቲቢ 2 የተባለ ለወታደራዊ አገልግሎት የሚውል መሆኑን ቢቢሲ ከጦርነት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ከሚተነትኑ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ማረጋገጡን በዘገባው አስነብቧል።

ሲባይላየን የተሰኘው እና በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን ባደረገው ተቋም የሚሠሩት ቤኔዲክት ማንዚን ደግሞ የተሰራጨውን ምስል በማየት “ንብረትነቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሆነ ቲቢ2 ባይራክተር ነው” ሲሉ እንደነገሩት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በሆሮጉዱሩ ወድቋል ስለተባለው ስለዚህ ሰው አልባ አውሮፕላን እስካሁን ድረስ ያለው ነገር እንደሌለ ዘገባው ጠቁሟል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለቱም ባለሙያዎች ሰው አልባ አውሮፕላኑ በመሳርያ ተመትቶ ስለመውደቁ የሚያሳይ ምንም ፍንጭ በምሥሉ ላይ እንደሌለ አረጋግጠዋል ብሏል።

የሲባይላየን (Sibylline) ድርጅት ባለሙያው ቤኔዲክት ደግሞ “ተመትቶ ስለመውደቁ የሚያሳይ ምንም ዓይነት መረጃ የለም፤ ሰው አልባ አውሮፕላኑ ሙሉ በሙሉ አልወደመም፤ የደረሰበት ትልቅ ጉዳት በፍጥነት እየበረረ ባለበት ወቅት በመከስከሱ የመጣ ነው” ሲሉ እንደገለጹለት ዘገባው አስነብቧለ።

“በአነስተኛ መሳርያ ተመትቶ ቢሆን እንኳ በአካሉ ላይ ጭረት መታየት ነበረበት” ማለታቸውንም አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተጋራው ምሥል ላይ ከወደቀው ባይራክተር ቲቢ 2 ድሮን ጎን ሁለት ያልፈነዱ ሚሳኤሎች እንደሚታዩ የጠቆመው ዘገባው የቢቢሲ ቬሪፋይ ቡድን አባላት ሁለቱ ሚሳኤሎች ሰው አልባ አውሮፕላኑ ታጥቋቸው የነበሩ ኤምኤኤም-ኤል (MAM-L) የተሰኙ ሚሳኤሎች መሆናቸውን እንዳረጋገጡ አስታውቋል።

የወደቀው ሰው አልባ አውሮፕላኑ አራት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ወይንም ሮኬቶችን የመታጠቅ አቅምም እንዳለው የጠቆመው ቢቢሲ ከ5 እስከ 6 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ የተተመነለት መሆኑን እና የሚያስወነጭፋቸው ሮኬቶች የእያንዳንዳቸው ዋጋ ከ 60,000 እስከ 100,000 ዶላር አንደሚገመት አመላክቷል። ይህም ማለት እያንዳንዱ ድሮን ታጥቆ የሚሰማራው ሚሳኤሎች ዋጋ 3.5 ሚሊዮን ብር ይገመታል ማለት ነው ብሏል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button