ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በትግራይ የሰላም ስምምነት ከተደረሰ ወዲህ 1329 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸውን በክልሉ የተደረገ ጥናት አመላከተ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15/2016 .ም፡ በትግራይ ባሰለፍነው አመት መጀመሪያ ወራት በፌደራል መንግስቱ እና በትግራይ ሀይሎች መካከል የሰላም ስምምነት ከተደረሰ ወዲህ 1329 ሰዎች በረሃብ ምክንያት መሞታቸውን በክልሉ የተደረገ ጥናት ማመላከቱን አሶሼትድ ፕረስ በዘገባው አስታወቀ።

የክልሉ የጤና ቢሮ ከመቀለ ዩኒቨርስቲ ጋር በጋራ ባካሄዱት ጥናት በትግራይ ዋነኛው የሞት መንስኤ ረሃብ ሁኖ መገኘቱን ያስታወቀው ዘገባው በጥኙወቹ ልየታ መሰረት ከ68 በመቶ በላይ የክልሉ የሞት መንስኤ ረሃብ መሆኑን ጠቁሟል።

ጥናቱ የተካሄደው በጤና ባለሞያዎች ከነሃሴ 9 እስከ ነሃሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም በክልሉ በሚገኙ ዘጠኝ ወረዳዎች ቤት ለቤት በመዞር እና በ53 የመጠለያ ካምፖች በሚገኙ ተፈናቃዮች ባካሄዱት ቆጠራ መሆኑን ያመለካተው ዘገባው በክልሉ በረሃብ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በጥናቱ ከተገለጸው በላይ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል።

በረሃብ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች እንዲጨምር የረድኤት ተቋማት የእርዳታ አቅርቦታቸውን ማቋረጣቸው ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተጠቁሟል። የጥናቱ ውጤት እንደሚያመላክተው ከሆነ የእርዳታ አቅርቦቱ ተቋረጠ በኋላ በክልሉ በረሃብ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን ዘገባው አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button