ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል ከ2.4 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችና ተፈናቃዮች የዕለት ድጋፍ እንደሚፈልጉ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7/ 2016 ዓ/ም፡_ በአማራ ክልል ከ2 ሚሊየን 400 ሺህ በላይ የዕለት ድጋፍ የሚሹ አርሶ አደሮችና ተፈናቃዮች መኖራቸውን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን ገለጸ። 

የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወ/ሮ ፍቅሬ ሙሉጌታ፤ በክልሉ በተፈጥሮ አደጋ ሰብላቸው የወደመባቸው ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን በላይ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ለፋና ተናግረዋል

በተጨማሪም ከ600 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች የዕለት ድጋፍ የሚሹ መሆኑን ኮሚሽኑ በልይታ አረጋግጧል ነው ያሉት፡፡ በተፈጥሮ አደጋ ሰብላቸው የወደመባቸው እና ተፈናቃዮች በክልሉ ዘጠኝ ዞኖች እና 43 ወረዳዎች እንደሚገኙም አንስተዋል፡፡

በ2015/16 የመኸር እርሻቸው የወደመባቸው የዕለት ድጋፍ የሚሹ የሰሜን ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች ድጋፍ ያልቀረበላቸው መሆኑን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ቅሬታ አቅርበዋል።

የአርሶ አደሮቹን ቅሬታ በተመለከተም ችግሩ መኖሩን አምነው፤ ይህም በአካባቢው ባለው “የሰላም እጦት ምክንያት በተከሰተ የትራንስፖርት ችግር” የተፈጠረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊዋ ባለፉት 6 ወራት ከፌዴራል መንግስት የተመደበ ከ307 ሺህ ኩንታል በላይ የዕለት ምግብ ለማቅረብ ቢሞከርም ድጋፍ ፈላጊዎችን ሙሉ በሙሉ ማዳረስ እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

ችግሩን በመፍታት ለተጎጂዎች የዕለት ደራሽ ምግብ ለማሰራጨ ትኮሚሽኑ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በክልሉ ለመጠባበቂያ ከተያዘ የምግብ ክምችት ውስጥ ከ38 ሺህ ኩንታል በላይ እህል ለ281 ሺህ ድጋፍ ፈላጊዎች መድርሱን የጠቀሱት ሃላፊው ክልሉ ከ430 ሚሊየን ብር በላይ መድቦ የዕለት ደራሽ ምግብ ገዝቶ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዚህ ቀደም የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ኮሚሽን በክልሉ 6.7 ሚሊዮን ሰዎች አረዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ማስታወቁ ይታወሳል። 

በክልሉ በ9 ዞኖች በተከስተው ድርቅ ምክንያት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድጋፍ እንደሚሹ የክልሉ የአደጋ መከላከል፣ ምግብ ዋስትና እና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ማስተባበሪያ ኮሚሽን በታህሳስ ወር አስታውቅቋልአስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button