ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ኢትዮጵያ ብሔራዊ የህፃናት እና የፍልሰት ፖሊሲ እያዘጋጀች መሆኑ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19/2016 ዓ.ም፡- የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች የተሳተፉበት በሀገራት መካከል የህገ ወጥ ፍልሰትን መከላከል ላይ ያተኮር አውደ ጥናት በአዲስ አበባ መካሄዱን ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

አውደ ጥናቱ በምስራቅና በአፍሪካ ቀንድ በሚገኙ ሀገራት መካከል ደህንነቱ የተጠበቀ የድንበር ተሻጋሪ ህፃናት ጉዳይ አያያዝን በተመለከተ ለመምከር የተዘጋጀ መሆኑን የጠቆመው መጃው በመደረኩ ላይ የተሳተፉት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ሁሪያ አሊ ድንበር ተሻጋሪ ህገ ወጥ የህፃናት ፍልሰት ተጨማሪ አደጋ ይዞ ከመምጣቱ በፊት ሀገራት በትብብር ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን አስታውቋል።

ህፃናት ለዳግም ስደት ጭምር እየተዳረጉ ለጉልበት ብዝበዛ፣ ለአካላዊ እና ፆታዊ ጥቃት እየተጋለጡ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ በህገ ወጥ ፍልሰት ውስጥ ህፃናት በራሳቸው መወሰን ሰለማይችሉ ጉዳዩ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ መናገራቸውን አካቷል።

ይህንን ለመቆጣጠር ኢትዮጵያ ብሔራዊ የህፃናት እና የፍልሰት ፖሊሲ እያዘጋጀች መሆኑንም አብራርተዋል ብሏል።

በተጨማሪም መድረኩ ህገወጥ የህፃናት ፍልሰት ጉዳይን በብሄራዊ የህጻናት ጥበቃ እና አያያዝ ስርዓት እንዲሁም በብሄራዊ ስደት ፖሊሲዎች ውስጥ ለማካተት እንደ ግብዓት ያገልግላል ተብሏል።

በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሚስስ አቢባቶ ዋኔ በበኩላቸው ፍልሰተኛ ህጻናት ሰብዓዊ መብታቸውና ደህንነታቸው በተጠበቀበት አግባብ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ብሎም ወደ ቤተሰብና ወደ ማህበረሰቡ ለማቀላቀል የሚከናወኑ ተግባራትም ስኬታማ እንዲሆኑ የበኩሉን እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

በመድረኩ ላይ የዓለም አቀፉ የህፃናት መርጃ ድርጅት፣ ዩኒሴፍ፣ የአለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት፣ የደቡብ አፍሪካ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ እና የመን ተወካዮች መሳተፋቸውን አመላክቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button