ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: ከአላማጣ እና አከባቢዋ ተፈናቅለው ቆቦ እና ሰቆጣ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺ መሻገሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15/2016 ዓ.ም፡- በቅርቡ በራያ አላማጣ አከባቢ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ከቀያቸው ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እና በዋግ ህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺ በላይ መሆኑን  የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የተፈናቃዮቹ ቁጥር ያገኘሁት ከሁለቱ ዞኖች አስተዳደር ነው ያለው የቢሮው መግለጫ በአከባቢው ከሚያዚያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረው አለመረጋጋት እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ሪፖርት የተደረገ ተፈናቃዮች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ አስታውሷል።

በቆቦ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ተፋናቃዮች ቁጥር 42 ሺ መድረሱን የጠቆመው ቢሮው በሰቆጣ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር 8 ሺ 300 መሆኑን ገልጿል።

አብዘሃኛዎቹን ተፈናቃዮች የቆቦ ከተማ ማህበረሰብ አስጠልሏቸው እንደሚገኝ የጠቆመው ቢሮው ሌሎቹ ደግሞ ከከተማዋ በሶስት ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ጋሪያ ሌንጫ በተባለ ሜዳ ላይ መጠለያ ዘርግተው እየኖሩ መሆኑን ገልጿል።  የዝናብ ወራት እየመጣ በመሆኑ ለዘርፈ ብዙ ችግር ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁሟል።

ተፋናቃዮቹን ወደ ተሻለ ቦታ ለማዘዋው ጥረት እየተደረገ መሆኑን አመላክቷል።

ከሚያዚያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሩ በቆቦ እና አላማጣ በአከባቢው አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን ያስታወቀው ቢሮው መሰረታዊ አገልግሎቶች ባንክ እና ትራንስፖርት መኖሩን ጠቁሟል። ከወልድያ እስከ ሰቆጣ ባለው መንገድ ግን በጸጥታ ችግር ምክንያት አስጊ በመሆኑ ትራንስፖርት ማግኘት አዳጋች ነው ሲል ገልጾ በሰቆጣ ተጠልለው ስለሚገኙ ተፈናቃዮች በቂ መረጃ ማግኝት እንዳዳገተው አስታውቋል።

በአከባቢው ውጥረት ተፈጥሯል ያሉ እና መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የሰባት ሀገራት ኤምባሲዎች ሁኔታው አሳሳቢ ነው ማለታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የካናዳ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣሊያን፣ ጃፓን፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል “አጨቃጫቂ ቦታዎች” ሲሉ በገለጿቸው የደቡብ ትግራይ አከባቢዎች የተፈጠረው ውጥረት አስግቶናል ማለታቸው በዘገባው ተካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button