ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሃፊ አንቶኒ ብሊንከን በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ገልፁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 29 /2015 ዓ.ም፡- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ዋና ጸሃፊ አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር በኢትዮጵያ ሰላም፣ ብፅግናና መረጋጋት ላይ ያተኮረ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ አስታወቀ፡፡ 

ብሊንከን  በሰሜን ኢትዮጵያ የጦርነት ማቆም ስምምነትን በመተግበር ረገድ መሻሻል መኖሩን ጠቁመው በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያለው ሁኔታ ግን እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ብሊንከንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የምግብ ዕርዳታን በፍጥነት ለማስጀመር የጋራ ግብን ለማሳካት የሰብአዊ ርዳታ ስርጭት ስርዓትን በተጠናከረ ሁኔታ ለመዘርጋት ያለመ ውይይት ማድረጋቸውን የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ መ/ቤቱ ጠቅሷል።

የአፍሪካ ቀንድን በተመለከተ ዋና ጸሃፊው በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ ለሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ አገራቸው አሜሪካ ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል።

አንቶኒ ብሊንከን በሱዳን ያለውን ቀውስ ለመፍታት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላደረጉት ቀጠናዊ ጥረቶች አድናቆታቸውን ገልፀዋል ሲል ተሸሽሎ በወጣው መግለጫ ላይ ተመላክቷል።አስ

Note: የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቀድሞ ያወጣውን መግለጫ በመቀየሩ ይህ ዜና በአዲሱ መግለጫ መሰረት የተስተካከለ መሆኑን እንደልፃለን፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button