ህግ እና ፍትህዜና

ዜና፡ በአማራ ክልል በስደተኞች መጠለያ አካባቢ በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሁለት ሱዳናውያን ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15/2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን በሚገኘው አውላላ የሥደተኞች መጠለያ ጣቢያ አከባቢ ሰፍረው በነበሩ ስደተኞች ላይ ቅዳሜ ዕለት በተፈፀመ ጥቃት የሁለት ሱዳናውያን ስደተኞች ህይወት ማለፉና 10 ስደተኞች መቁሰላቸውር ተገለጸ::

የአውላላ ካምፕ ምንጮች ለሱዳን ሚዲያ እደገለጹት ከሆነ የታጠቁ ሰዎች በስደተኞቹ ላይ ጥቃት የፈጸሙ ሲሆን በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል:: በጥቃቱ ሌሎች 10 ስደተኞችም መቁሰላቸውም ተገልጿል::

ጥቃቱ የደረሰው የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኮሚሽን ተወካዮች አካባቢውን ጎብኝተው ከሄዱ በኋላ መሆኑ ተነግሯል::

ከዚህ ቀደም ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም በአማራ ክልል በሱዳናውያን መጠለያ ካምፕ አቅራቢያ በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች እና በታጣቂዎች መካከል በተደረገ ውጊያ ዘጠኝ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መገደላቸውንና ስደተኞች መጎዳታቸውን ይታወቃል::

ስደተኞቹ በታጣቂዎች ጥቃቶች እንደተፈጸሙባቸው እና በትጥቅ የታገዙ ዘረፋዎች እንዲሁም ለገንዘብ የሚደረጉ እገታዎች ተደጋጋሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ተከትሎ መጠለያ ካምፖቹን ጥለው በአቅራቢያቸው በሚገኘው ጫካ መኖር መጀመራቸውን መዘገባችን ይታወሳል። 

በግንቦት ወር ወደ 1000 የሚሆኑ ስደተኞች ኩመር እና አውላላ ካምፖችን ለቀው ወጥተዋል።

በአማራ ክልል በምዕራብ ጎንደር ዞን የሚገኙት አውላላ እና ኩመር የተሰኙት የተመድ መጠለያ ጣቢያዎች ከሱዳን፣ ከኤርትራ እና ከደቡብ ሱዳን የሚመጡ ስደተኞችን ይቀበላሉ።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይሁንና በአከባቢው በተፈጠረው ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት ምክንያት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ድርጅት በአማራ ክልል የስደተኞች ካምፕ ላይ ተጠልለው የሚገኙ ሱዳናውያንን ስደተኞችን ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር መወሰኑን አስታውቋል።

ይህን ተከትሎም የተባበሩት መንግሥታት የሥደተኞች ድርጅት (UNHCR) በአከባቢው የሚገኙ ስደተኞች ወደ ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ እያዘዋወረ እንደሚገኝ ተገልጿል:: አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button