ቢዝነስዜና

ዜና፡ መንግሥት ባለፉት 15 ወራት ከ23 ቢሊየን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን አስታወቀ፣

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24/2016 ዓ.ም፡- መንግስት የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ ከተደረገበት ሐምሌ ወር በ2014 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከ23 ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር በላይ ለተሽከርካሪዎች ድጎማ ማድረጉን አስታወቀ።

በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ብሔራዊ የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰልማን መሀመድ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት በተያዘው ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከስድስት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ ለተሽከርካሪዎች ድጎማ ማድረጉን ጠቁመው መንግሥት ድጎማ ማድረግ ከጀመረበት ግዜ አንስቶ ባሉት ያለፉት 15 ወራት ከ23 ቢሊየን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን አመላክተዋል።

መንግሥት የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎችን በመለየት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን ሃላፊው አስታውቀው በድጎማ ሥርዓቱ የሚካተቱ ተሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን እና የነዳጅ ድጎማ ሥርዓቱ ከተዘረጋ አንስቶ እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ 240 ሺህ 890 ተሽከርካሪዎች ወደ ዲጂታል ሥርዓቱ መግባታቸውን ጠቁመዋል። በሩብ ዓመቱ ዘጠኝ ሺህ 872 ተሽከርካሪዎች ለድጎማ መመዝገባቸውንም ገልጸዋል።

በአዲስ አበባና በሁሉም የክልል ከተሞች ተሽከርካሪዎች በሥርዓቱ እንዲመዘገቡ ተደርጓል ያሉት አቶ ሰልማን፤ በአጠቃላይ ከተመዘገቡት ተሽከርካሪዎች ውስጥ 197 ሺህ 454 የሚሆኑት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ መሆናቸውን እና ከዚህ ውስጥ ከ20 ሺህ በላይ የሚሆኑት ተሽከርካሪዎች በሩብ ዓመቱ የድጎማ ተጠቃሚ የተደረጉ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ ማድረጋቸውን አስታውሰው በዚህም እስከ መስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከ81 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button