ቢዝነስዜና

ዜና፡ ኤም ፔሳ የዲጂታል መገበያያ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን የኢትዮጵያ ደንበኞች ማፍራቱን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም፡- የሳፋሪኮም ቴሌኮም ኩባንያ የዲጂታል መገበያያ የሆነው ኤም ፔሳ በኢትዮጵያ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ደንበኞች ማፍራቱን አስታወቀ።

የፈረንጆቹ ዘመን አቆጣጠር የ2023 የግማሽ አመቱን ትርፍ ይፋ ባደረገበት የኩባንያው የዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2016 ዓ.ም መግለጫው በኢትዮጵያ ከሁለት ወራት በፊት ያስተዋወቀው የዲጂታል ገንዘብ መገበያያ 43 ነጥብ 7 ቢሊየን የኬንያ ሽሊንግ ወይንም ከ288 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ግብይት ማከናወኑን አመላክቷል።

ኤም ፔሳ ነሃሴ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ በይፋ የዲጂታል ግብይቱን ማስጀመሩ ይታወሳል።

ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት በሚሰጥባቸው 22 ከተሞች ከ4 ነጥብ አንድ ሚሊየን በላይ ደንበኞች ማፍራቱን አስታውቋል።

ኤም ፔሳ በኢትዮጵያ 23ሺ ወኪሎች እና 12ሺ ነጋዴዎች በዲጂታል የግብይት ስርአቱ አገልግሎት በመጠቀም ላይ መሆናቸውንም በመግለጫው አመላክቷል።

‘’ይህ ስኬታችን ስለኢትዮጵያ ስንገልጽ የነበረውን ምን ያክል እውነት መሆኑን የሚያረጋግጥል ነው፣ በአመቱ የመጀመሪያው አጋማሽ የተገኘውን ስኬት አስጠብቀን በሁለተኛው የአመቱ አጋማሽ እናጠናክረዋለን’’ ሲሉ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ፒተር ንዲግዋ ገልጸዋል።

‘’በኢትዮጵያ አሁን ባለን አነስተኛ መሰረት የኤም ፔሳ እና የዳታ በኩል የሚታየው አጠቃቀም ተስፋ እጅግ ትልቅ ነው፣ በተለይም በሞባይል ዳታ አጠቃቀም ላይ ያየነው ፍላጎት እጅግ አርክቶናል፤ የዚህ አይነት የዳታ ፍላጎት ኩባንያው ያየው በኬንያ ስራ ከጀመረ አስር አመታት በኋላ ነው‘’ ሲሉ ስራ አስፈጻሚው ተናግረዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ፍቃድ ለሳፋሪኮም የቴሎኮም ኩባንያ የሰጠው ባሳለፍነው አመት ግንቦት ወር መጀመሪያ መሆኑ ይታወሳል። ኤም ፒሳ በሚል የሞባይል ስልክ የግብይት አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው ሳፋሪኮም በኢትዮጵያ በዘርፉ ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የውጭ ኩባንያ እንዳደረገው በወቅቱ ተዘግቧል። አስ    

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button