ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች የትምህርት ሚኒስቴር ያቀረበውን የሴት ተማሪዎች የወሊድ ፍቃድ ረቂቅ መመሪያን እንደገና እንዲያጤነው ጠየቁ 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21/ 2016 ዓ/ም፦ የትምህርት ሚኒስቴር “አንድ ተማሪ በወሊድ ምክንያት 16 ቀናትና ከዚያ በላይ ከትምህርት ገበታዋ ከቀረች ከዘመኑ ትምህርት እንድትታገድ” የሚያደርገውን ረቂቅ መመሪያን እንደገና እንዲያጤነውና በፍጥነት ማስተካከያ እንዲያደርግ በሴቶች መብት ዙሪያ የሚሰሩ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ጠየቁ።

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት እና የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች ጨመሮ 10 የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የትምህርት ሚኒስቴር ረቂቅ መመሪያን በተመለከተ ትላንት ህዳር 20 በጋራ መግለጫ አወጥተዋል።

ድርጅቶቹ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው ረቂቅ መመሪያ ከፍል አራት፣ አንቀጽ 15፣ ተራ ቁጥር 5 መሰረት ያወጣው ረቂቅ መመሪያ ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ሴቶች የወሊድ ፈቃድ መብትን በእጅጉ የሚገድብ መሆኑን ገልጸዋል። ከዚህም ባለፈ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን አወንታዊ የድርጊት ድንጋጌዎች “የሚንድና የሴቶችን መሠረታዊ የመማር መብቶች በግልጽ የሚነፍግ ነው” ብለዋል። በተጨማሪም እድል ለመስጠት የተጀመረውን አካታች አካሄድ የሚያደናቅፍና ወደኋላ የሚጎትት አካሄድ ነው ሲሉም ተቃውመዋል፡፡ 

የወሊድ ፈቃድ መከልከል እና ሴቶች ትምህርታቸውን እንዳይቀጥሉ አማራጮችን መገደ በሴቶች የትምህርት እንቅስቃሴዎች ላይ ተጨማሪ እንቅፋቶችን መፍጠር ነው ያሉት ድርጅቹ ይህ ረቂቅ መመሪያም ለሴቶች ሌሎች አማራጮችን ከመፍጠር ይልቅ እንዳይበቁና በህብረተሰቡ ውስጥ ሙሉ በሙሉ መሳተፍ እንዳይችሉ የሚያደርግ ቀጥተኛ ጥቃት ነው በለዋል።

የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶቹ ረቂቅ መመሪያው የሴቶች እና የወንዶች በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊ እና በፖለቲካዊ ዘርፎች እኩልነትን የሚጥስ ከመሆኑም በላይ ሴቷ ትምህርትን፣ ስራን፣ የሀብት ተደራሽነትን እና አስተዳደርን የማግኝነት መብቷን የሚጥስና የሚቃረን በመሆኑ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ይህን ረቂቅ መመሪያ በፍጥነት ማስተካከያ እንዲደረግበት ጠይቀዋል። 

በተጨማሪም ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትም ባቀረቡት ጥሪ ረቂቅ መሪያው ላይ ተገቢው የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድበት ጠይቀዋል።

ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ዓመለወርቅ ህዝቅኤል መመሪያው ገና የመጀመሪያው ረቂቅ ላይ መሆኑን ገልጸው ወደ ትግበራ አልገባም ሲሉ ለኢቢሲ ሳይበር ሚዲያ ተናግረዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ረቂቁን ያዘጋጁት ሰዎች የተለያዩ አስተያየቶችን እንደሚቀበሉ የገለጹት ዳይሬክተሯ፣ ረቂቅ መመሪያው ብዙ ሒደቶች እንደሚቀሩት ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button