ዜናጤናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ሚስጥራዊ ሴራ አሲረውባቸው እንደነበር ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያው ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ባላንጣነታቸው የተካረረ መሆኑን ብሉምበርግ በድረገጹ ባስነበበው ሃተታ አስታውቋል። ሁለቱም በፕላኔታችን የሚገኙ ምርጥ አፍሪካዊ መሪዎች ናቸው ሲል ብሉምበርግ በሃተታው የገለጻቸው አብይ አህመድ እና ቴዎድሮስ አድሃኖም በሁለት ጎራ ቆመው በባላንጣነት መተያየት ከጀመሩ መሰንበታቸውን ጠቁሞ በዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ሚስጥራዊ ሴራ አሲረው እንደነበር ያገኛቸው ሚስጥራዊ የኢትዮጵያ መንግስት ሰነዶች ማመላከታቸውን አስታውቋል።

ዶ/ር አብይ አህመድ እና መንግስታቸው የአለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተሩ በኢትዮጵያ ባለስልጣን ሁነው ባገለገሉበት ወቅት ከፍተኛ ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ክስ አዘጋጅቶባቸው እንደነበር ድረገጹ ባስነበበው ሃተታ ገልጿል። ክስ ሊመሰረትባቸው የነበረውም የመንግስትን እና የህዝብን ሃብት ያላግባብ በመጠቀም የሚል እና ከወሲብ ጋር የተገናኘ ያልተገባ ተግባር የሚሉት እንደሚገኙበት ተጠቁሟል።

ምርመራው ይካሄድ የነበረው እና ክስ ሊመሰረት የነበረው ዶ/ር ቴዎድሮስ የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት በድጋሚ ለመመረጥ ዘመቻ በጀመሩበት ወቅት እንደነበር ብሉንበርግ አስታውሷል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ በበኩላቸው ሁሉንም ክሶች ማስተባባላቸውን ያስታወቀው ብሉንበርግ ምንም አይነት ክስ በመንግስት በኩልም እንዳልተመሰረተባቸው አስታውቋል። የአለም የጤና ድርጅት ዳይሬክተሩ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ እንደማይፈልጉ እና የሚመለሱም ከሆነ ከመንግስት የደህንነት ማስተማመኛ ከተሰጣቸው ብቻ መሆኑን እንደነገሩት ድረገጹ በሃተታው አመላክቷል።

የሁለቱም ታላላቅ ሰዎች ግንኙነት የተበላሸው የትግራዩ ጦርነት መጀመሩን ተከትሎ መሆኑን ሃተታው አውስቷል። በኢትዮጵያ የሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ላይ የመንግስት የደህንነት ሰዎች እንደሚያንገላቷቸው ዶ/ር ቴዎድሮስ ነግረውኛል ያለው ብሉንበርግ በጀኔቫ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ የኢትዮጵያ መንግስት የደህንነት ሰዎች እያንዣበቡ ስላሰጓቸው የደህንነት ካሜራ እስከ ማስገጠም መድረሳቸውን ጠቁሟል።

በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ ክስ ለመመስረት በመቶወች የሚቆጠሩ ሰነዶች በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ተዘጋጅቶ ለፍትህ አካላት መላኩን እና የተላኩትን ዶክመንቶች ለመመልከት መቻሉን ያስታወቀው ብሉንበርግ ክስ ለመመስረት ተዘጋጅተው ከነበሩ ጉዳዮች መካከል ዶ/ር ቴዎድሮስ የሀገሪቱ የጤና ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት የተወሰኑ የህክምና አቅራቢዎች ያለአግባብ ጨረታ እንዲያሸንፉ ማድረግ የሚል እንደሚገኝበት ጠቁሟል። ለዚህ ክስም እንደማስረጃነት የባንክ ሰነድ፣ በእጅ የተጻፉ መረጃዎች እና የተለዋወጧቸው የኢሜይል መልዕክቶች መቅረባቸውን አስታውቋል።

ዶ/ር ቴዎድሮስ ያለአግባብ ስልጣናቸውን ተጠቅመው የአለም የጤና ድርጅት ካወጣው መስፈርት የማያሟላ የኤችአይቪ ኤድስ መመርመሪያ ኪት እንዲገዛ አድርገዋል የሚል ክስ ሊቀርብባቸው እንደነበር ከዶክመንቶቹ መረዳቱን ብሉንበርግ ጠቁሟል። ክሱ በመጀመሪያ ደረጃ የቀረበው አጽበሃ ገ/እግዚያብሄር በተባሉ የሀገሪቱ የጤና ኢኒስቲትዩት ተመራማሪ እንደነበር የገለጸው ድረገጹ አጽብሃ በስልክ በሰጡት አስተያየት ከደረጃ በታች የሆኑት የኤችአይቪ መመርመሪያዎቹ ኪቶች ግዢ የተፈጸመው ዶ/ር ቴዎድሮስ የጤና ሚኒስትርነትን ለቀው ወደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ገተዛወሩ በኋላ መሆኑን መግለጻቸውን ዘገባው አካቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button