ፖለቲካ

ዜና: 25 ዩኒቨርስቲዎች የበጀት ዕቅዳቸውን አስተካክለው በሶስት ቀናት ውስጥ እንዲያቀርቡ ትእዛዝ ተሰጣቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም፡- የገንዘብ ሚኒስቴር ትላንት ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም የኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጀት ስሚ መርሀ-ግብር ማካሄዱን አስታወቀ።

በከፍተኛ ትምህርት የክላስተር አደረጃጀት 21 የኮምፕርሄንሲቭ፣ ሁለት የሳይንስና ቴክኖሎጅ እንዲሁም ሁለት የልዩ ዩኒቨርሲቲዎች የ2017 በጀት ዕቅድ ትላንት ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም በገንዘብ ሚኒስቴር ቀርቦ መገምገሙ ተገለጸ።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ የዩኒቨርሲቲዎችን የበጀት ስሚ መርሀ-ግብር ሲከፍቱ ባደረጉት ንግግር የዩኒቨርሲቲዎች በጀት በተለይም የፕሮጀከት ወጭዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናሩ በመምጣታቸው ተገቢው ቁጥጥር ሊደረግባቸው እንደሚገባ አመልክተዋል።

በአፈጻጸማቸው የተሻሉትን ፕሮጀክቶች ለይቶ ማጠናቀቅ እና ዝቅተኛ አፈጻጸም ኖሯቸው የተቋረጡትን ደግሞ ባሉበት እንዲቆዩ ማድረግ የመጭው ዓመት የበጀት አቅጣጫ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከባለፈው በጀት ዓመት በተለየ መልኩ ዘንድሮ “አፕላይድ”፣ “ኮምፕርሄንሲቭ”፣ “ሳይንስና ቴክኖሎጅ” እንዲሁም “ልዩ” በሚለው የከፍተኛ ትምህርት የክላስተር አደረጃጀት መሰረት በቀጣዩ በጀት ላይ ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት ማድረግ አስፈላጊ ነው ሲሉ ሚኒስትሩ አሳስበዋል።

በበጀት ስሚው መርሀ-ግብር የተገኙት የገንዘብ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኢዮብ ተካልኝ በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውድድር በሚመስል መልኩ ከትምህርት ጥራት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ከሌላቸው የግንባታ ፕሮጀክቶች ወጥተው የተመደበላቸውን በጀት በዋናው የመማር ማስተማር ተልዕኳቸው ላይ ሊያውሉት ይገባል ብለዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙት ሁሉም የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንቶች ሃሳባቸውን በየተራ እንዲያንሸራሽሩ ከተደረገ በኋላ በሚኒስቴሩ ባለሙያዎች የተሰጣቸውን ዝርዝር አስተያየቶች በማካተት የበጀት ዕቅዳቸውን አስተካክለው በሶስት ቀናት ውስጥ እንዲያቀርቡ ተገልጾላቸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በተመሳሳይም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት የ2017 የበጀት ዕቅድ ቀርቦ ውይይት እንደተደረገበት ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

የበጀት ዕቅዱ ከተገመገመ እና ሰፊ የሃሳብ ልውውጥ ከተካሄደ በኋላ ተቋማቱ በተሠጣቸው ጣሪያ መሰረት፣ የተመደበላቸውን በጀት በቁጠባና ውጤታማነት መርህ፣ ቅድሚ ለሚሰጡ ጉዳዮች ቅደም ተከተል አስይዘው፣ በሶስት ቀናት ውስጥ ለገንዘብ ሚኒስቴር እንዲያቀርቡ መግባባት ላይ መደረሱን መረጃው አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button