ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በአማራ ክልል የመማሪያ መጻህፍት በወቅቱ ታትመው ባለመቅረባቸው በትምህርት ጥራት ላይ ሌላ ፈተና መፍጠራቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20/2016 ዓ.ም፡- በአማራ ክልል የመማሪያ መጻህፍት በወቅቱ ታትመው ባለመቅረባቸው በትምህርት ጥራት ላይ ሌላ ፈተና እንደሆነባቸው የክልሉ መምህራን እና የትምህርት ባለሙያዎች አስታወቁ።

መማሪያ መጻሕፍት በወቅቱ ተሟልተው ባለመቅረባቸው በትምህርት ሥርዓቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩን አሚኮ ያነጋገራቸው የክልሉ የትምህርት ባለሙያዎች ገልጸዋል።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከሚማሩባቸው ከአስር የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ሦስቱ ታትመው ባለመቅረባቸው አሁንም ድረስ ትምህርት አለመሰጠቱን የወረዳው ከሚገኙ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አንዱ በሆነው ነው አሁጫራ ቀበሌ የአረባይ ርዕሰ መምህር ተመስገን ተካ መናገራቸውን ዘገባው አካቷል።

ርዕሰ መምህሩ እንዳሉት በአካባቢው የተከሰተው ድርቅ በመማር ማስተማር ሥራው ላይ ፈተና ቢኾንም የመማሪያ እና ማስተማሪያ መጻሕፍት ተሟልተው አለመቅረብም በትምህርት ሥራው ላይ ሌላ ችግር ፈጥሯል። እስከ አሁንም “ከአስሩ የትምህርት ዓይነቶች ውስጥ ሰባቱን የትምህርት ዓይነቶች ብቻ ነው ተማሪዎች እየተማሩ የሚገኙት” ብለዋል፡፡

የግብረ ገብ፣ ሙያና ቴክኒክ እንዲሁም አይሲቲ የትምህርት ዓይነቶች መጻሕፍት ታትመው ባለመቅረባቸውን እና እነዚህን ትምህርት ዓይነቶች የሚያስተምሩ መምህራን አለመመደባቸውንም ገልጸዋል።

በእጥረት የተነሱት የአንደኛ ደረጃ መማሪያ መጽሐፍት በአንድ ለአራት ሂሳብ ታትመው በየክዘና ማዕከላት ከገቡ መቆየታቸውን የአማራ ክልል ትምህርትን ቢሮ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ዳይሬክተር ካሴ አባተ ገልጸዋል ያለው ዘገባው የመማሪያ መጽሐፍቱ እስከ አሁን ወደ ትምህርት ቤቶች ያልተሰራጨበትን ምክንያት ቢሮው እንደሚያጣራም መጠቆማቸውነ አስታውቋል።

የአማርኛ ቋንቋ መማሪያ መጽሐፍ መታተሙን ገልጸው በትራንስፖርት ችግር ወደ ትምህርት ቤቶች አለመሰራጨቱን በመግለጽ በቅርቡም ተደራሽ ይኾናል ማለታቸውን አመላክቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button