ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በጋምቤላ ተጠልለው የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ለምግብ ፍለጋ ሲንቀሳቀሱ በታጠቁዎች ተገድለዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21/2016 ዓ.ም፡- በጋምቤላ ክልል ከግንቦት ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ በነበሩ ግጭቶች እና ጥቃቶች በክልሉ በተለያዩ ቦታወች ተጠልለው የሚገኙ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ከፍተኛ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገለጸ።

በተለያዩ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በሚኖሩ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ላይ በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ እንዲሁም ከመጠለያ ጣቢያ ውጪ ለምግብ ፍለጋ እና ለተለያዩ ጉዳዮች ሲንቀሳቀሱ በታጠቁ ቡድኖች እና ግለሰቦች በደረሰ ጥቃት ብዙ ሰዎች መገደላቸውን እና የአካል ጉዳት መድረሱን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ባወጣው ሪፖርት አሰታውቋል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ስደተኞችም ጭምር በእነዚሁ ግጭቶች ተሳታፊ እንደነበሩ ነዋሪዎች እና የመንግሥት አካላትን ዋቢ በማድረግ ኮሚሽኑ ጠቁሟል።

የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ከደቡብ ሱዳን የመጡ ስደተኞችን ተቀብሎ የሚያስተናገድ እንደመሆኑ በስደተኞች እና ተቀባይ ማኅበረሰብ መካከል ግጭቶች በብዛት እንደሚነሱ አስታውቋል።

በክልሉ የሚነሱ አለመግባባቶችና ግጭቶችን ለመፍታት የክልሉ መንግሥት ከስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት (RRS) እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት በርካታ ሥራዎችን እያከናወነ ቢገኝም፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት በቂ የጸጥታ ኃይሎችን ግጭቶች በተደጋጋሚ በሚከሰትባችው ስፍራዎች በቋሚነት መመደብን ጨምሮ የሁሉም ባለ ድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረትን እንደሚሻ አሳስቧል።

የጋምቤላ ክልል መንግሥት በተለያየ ጊዜ ሰፊ እና ተደጋጋሚ የሰላም እና የዕርቅ ውይይቶች ማከናወኑ የጠቆመው ሪፖርቱ በወንጀል ድርጊት ላይ ተሳትፈዋል ተብለው የተጠረጠሩ የአስተዳደር አመራሮች እና የጸጥታ አባላት ተጠያቂነት የማረጋገጥ እርምጃዎችም መጀመራቸውንም ገልጿል።

ኢሰመኮ በተለያዩ የክልል ቦታዎች ቢያንስ የ138 ሰዎች ሕይወት ማለፉን፣ 113 ሰዎች ላይ አካል ጉዳት መድረሱን እንዲሁም በግለሰቦች እና ተቋማት ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥ መቻሉን በሪፖርቱ በዝርዝር አካቷል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኢሰመኮ ግጭት ወደተከተሰባቸው ቦታዎች በአካል በመሄድ ከተጎጂዎች፣ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከዐይን ምስክሮች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ከሃይማኖት መሪዎች ጋር ቃለ መጠይቆች እና የቡድን ውይይቶች ማድረጉንም አስታውቋል።

በተጨማሪም በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ መንግሥት የጸጥታና አስተዳደር አካላትን እንዲሁም የፌዴራል ተቋማትን በማነጋገር መረጃዎችንና ማስረጃዎችን ማሰባሰቡን ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button