ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በኢትዮጵያ ግድያዎች እና እገታዎች በተደጋጋሚ መፈጸማቸው መንግስት ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ እንዳልሆነ ማሳያ ነው – ኢሰመጉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚፈጸሙ እገታዎች እና ግድያዎች አፋጣኝ መፍትሄ ሊሰጣችው ይገባል ሲል ዛሬ የካቲት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ጠየቀ።

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ዜጎች ላይ በታጠቁ ቡድኖች እየተፈጸመ ያለው እገታ እና ግድያ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መጥቷል ሲል የገለጸው ኢሰመጉ ግድያዎች እና እገታዎች በተደጋጋሚ መፈጸማቸው መንግስት ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ እንዳልሆነ ማሳያ ነው ሲል ወቅሷል።

ይህም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሚገኙ ዜጎች ላይ ጭምር ስጋት እያሳደረ ይገኛል ብሏል።

በያዝነው የየካቲት ወር በዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም የተፈጸመ እገታ እና ግድያ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ጂሌ ጥሙጋ ወረዳ የተፈጸመውን ግድያ ኢሰመጉ በመግለጫው በማሳያነት አስቀምጧል።

በአከባቢዎቹ ለሚስተዋለው ችግር ዘላቂ መፍትሄ ባለመሰጠቱ ነዋሪዎቹ በእገታ እና በግድያ ስጋት ውስጥ እንዲኖሩ እያደረጋቸው ይገኛል ሲል ገልጿል።

የኢሰመጉ ባቀረበው ጥሪ የፌደራል መንግስት እየተፈጸሙ ላሉ የእገታ ድርጊቶች ተገቢውን በቂ ትኩረት እንዲሰጥ እና ፈጻሚዎችን ተጠያቂ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ህጎችና ፖሊሲዎችን እንዲያጸድቅ ጠይቋል።

የኦሮምያ ክልል መንግስት በክልሉ በታጣቂ ቡድኖች እየተፈጸመ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከማውገዝ ባለፈ ስር ነቀል ሁሉን አቀፍ ክትትል በማድረግ ወንጀለኞችን ለህግ እንዲያቀርብ ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ይመጣ ዘንድ በተለያዩ ቦታዎች የሚቀሳቀሱ ታጣቂ ቡድኖች ሰላማዊ መንገድን በመምረጥ የዜጎች ሰላም ይንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ይንዲወጡ ሲል አሳስቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button