ዜና

ዜና፡ “ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ” በማሰራጨት ወንጀል ተጠርጥሮ በዕስር ላይ የመገኘው ጋዜጠኛ እንዲፈታ ማህበሩ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት19/2016 ዓ/ም፦ የሶማሌ ጋዜጠኞች ማህበር ከሁለት ሳምንት በፊት የካቲት 5/ 2016 በክልሉ የፀጥታ አካላት የታሰረው ጋዜጠኛ ሞሀዲን መሐመድ በአስቸኳይ እንዲፈታ ጥሪ አቀረበ።

ከዚህ ቀደም በካልሳን ቴሌቪዥን፤ በአሁኑ ወቅት ደግሞ  በማህበራዊ ሚዲያ ጦማሪነት እየሰራ የሚገኘው ሞሀዲን፤ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ጅግጅጋ ከተማ መሄዳቸውን ተከትሎ “የአሳቸው መምጣት የትራፊክ መጨናነቅ አስከትሏል” በማለት በማህበራዊ ትስስር ገጹ በመለጠፉ ለዕስር መዳረጉን የማህበሩ ሊቀመንበር አብዱልርዛቅ ሀሳን ገልጸዋል። 

አብዱልረዛቅ በማከልም ሞሀዲን ያለ ምንም ክስ ለሰባት ቀናት ባልታወቀ እስር ቤት ታስሮ መቆየቱን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። ከዛ በኋላ ወደ ፋፋን ዞን ፖሊስ ጣቢያ የተላለፈ ሲሆን የካቲት 12 ፍርድ ቤት በማቅረብ “የሐሰት ፕሮፓጋንዳ በማሰራጨት”  ክስ ቀርቦበታል ብለዋል። ፍርድ ቤቱ ለፖሊስ 10 ምርመራ ቀን መስጠቱን አክለው ገልጸዋል።

“ያለበት እስር ቤት በመሄድ በቀን ሶስት ግዜ እየጎበኘነው ነው” ያሉት የማህበሩ ሊቀመንበር “አባሎቻችን ሙሃዲንን ለማስለቀቀ ጠበቆችን እያመከሩ ነው” ብለዋል።

ሙሃዲን  በሶማሌ ክልል ለእስር የተዳረገ ብቸኛ ጋዜጠኛ አየደለም። በአመት በፊት የካልሳን ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ሙሂያዲን ሞሃመድ መታሰሩን አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወቃል። እስሩ የተፈጸመው የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ፤ ህጋዊ ፍቃድ የላቸውም በሚል በክልሉ የሚሰሩ 15 የውጭ ሚዲያዎችን  ካገደ  ከአንድ ቀን ባኋላ ነው።

የክልሉ ካገዳቸው 15 የውጭ ሚዲያዎች ውስጥ ቢቢሲ ሶማሌ፣ ቪኦኤ ሶማሌ እና ካልሳን ቲቪ ይገኙበታል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button