ዜናፖለቲካህግ እና ፍትህ

ዜና፡ ኢሰመኮ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ጉዳት ያደረሱ አጥፊዎች ሊጠየቁ ይገባል ሲል አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10/2016 .ም፡ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ ጋሞ ዞን፣ በቆላ ሻራ ቀበሌ ውስጥ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች (የክልሉ ፖሊስ አባላት) እና በቀበሌው ነዋሪዎች መካከል የነበረውን አለመግባባት ተከትሎ ነዋሪዎች መሞታቸውን ንብረት መውደሙን አስታውቋል።

ለሟቾች ቤተሰቦች እና በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንዲሁም ንብረታቸው ለወደመባቸው ሰዎች፣ ለደረሰባቸው ጉዳት ተመጣጣኝ የሆነ ካሳ እንዲከፈል ሲል ጠይቋል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ተጠያቂነትን ከማረጋገጥና የተጎዱትን ከመካስ በተጨማሪም ለዚህና ተመሳሳይ ግጭቶች ምክንያት የሆነው የአካባቢ አስተዳደር መዋቅር ጥያቄና ውዝግብ ነዋሪዎችን ተዓማኒ በሆነ መንገድ ባሳተፈ ሰላማዊ ውይይት አፋጣኝ መፍትሔ ይሻል” ማለታቸውንም አመላክቷል፡፡

ኮሚሽኑ በአከባቢው በመገኘት ምርመራ ማከናወኑን አስታውቆ ከተጎጂዎች፣ ከዐይን ምስክሮች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ በፖሊስ ጣቢያ ተይዘው ከነበሩ ተጠርጣሪዎች፣ በተለያዩ መዋቅሮች ሥር ከሚገኙ የመንግሥት የአስተዳደር፣ የፍትሕ፣ የሰላምና ጸጥታ እንዲሁም የትምህርት መዋቅር ኃላፊዎች ጋር ቃለ መጠይቆችን እና የቡድን ውይይቶችን ማድረጉን አስታውቋል።

ለምርመራው አግባብነት ያላቸውን የሰነድ ማስረጃዎችን ከሆስፒታል፣ ከከተማ አስተዳደር ተቋማት እና ከተጎጂዎች ማሰባሰቡንም ጠቁሟል። በግጭቶቹ ሰዎች መሞታቸውን ንብረት መውደሙን ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button