ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በኡጋንዳ የሚገኙት ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ እንዲመለስ በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ትሰራለች አሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10/2016 .ም፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄዋ እንዲመለስ በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ መስራቷን እንደምትቀጥል ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑካን ቡድናቸው በኡጋንዳ፣ ካምፓላ እየተካሄደ በሚገኘው የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ርዕሳነ ብሔር እና ርዕሳነ መንግሥታት 19ኛው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛል፡፡

ጠ/ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት የህዝቦቻቸውን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተቸገሩ መሆናቸውን እና ከባድ ፈተናዎች እንደሚገጥማቸው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያም ይህን ችግር ለመፍታት በሰላማዊና በጋራ ተጠቃሚነት እንዲሁም በድርድር መፍትሄ ለማግኘት ጥረት እያደረገች መሆኑን በጉባኤው ላይ ማስረዳታቸውን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልጸዋል።

በተያያዘ ዜና ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ ጉባኤ ጎን ለጎን ከኬንያው ከፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ ጋር በቀጠናዊ እና ሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button