ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የምንሠራቸው ስራዎች ሀገርን የማዳን እና ለሌሎች መንገድ የማሳየት ነው ሲሉ ጠ/ሚኒስትር አብይ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 10/2016 .ም፡ ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ለብርሃነ ጥምቀቱ የእንኳን አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ የተጠመቀው ለሁለት አላማ ነው ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ አንደኛው ለሌሎች አርአያ ምሳሌ ለመሆን ነው ሁለተኛው ደግሞ አዳምን በየውድቀቱ ምእራፍ ለማንሣት ነው ሲሉ መልዕክታቸውን ጀምረዋል።

ክርስቶስ እስከ ጥምቀቱ ድረስ ባደረገው ጉዞ ሐዋርያት አልነበሩትም ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ያም ማለት ከ33 ዓመታት ውስጥ 30ውን ዓመት ሐዋርያት ሳይኖሩት ነው ያሳለፈው ማለት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ቀደም ብለን ያነሣናቸውን ሁለቱን ዓላማዎች ሐዋርያት ከመኖራቸው በፊት ይሠራ ነበር፤ ሐዋርያት ከመጡ በኋላም ይሠራ ነበር ብለዋል።

እስከ ዕለተ ጥምቀቱ የሠራው ሥራ በይፋ የተደረገ አልነበረም ሲሉ የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ ከጥምቀቱ በኋላ የሠራቸው ሥራዎች ግን በይፋ፣ በመገለጥ የተሠሩ ሥራዎች መሆናቸውን አስታውሰዋል።

የሁለቱ ልዩነት የዓላማና የተግባር አይደለም፣ በብዙ ሕዝብ በይፋ የመታወቅና ያለመታወቅ ጉዳይ እንጂ ሲሉ አስታውቀዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ አያይዘውም እንደ ሀገር የምንሠራቸው ሥራዎች ሁለት ዓላማ ያላቸው ናቸው ሲሉ ገልጸው ሀገርን የማዳንና ለሌሎች መንገድ የማሳየት መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ በብዙ ስብራቶች ውስጥ ያለፈች ሀገር ናት ሲሉ የገለጹት ጠ/ሚኒስትሩ ክርስቶስ ለአዳም እንዳዘነለት የሚያዝንላት ትፈልጋለች፣ ክርስቶስ ስለ አዳም ሆኖ ሸክሙን እንደተሸከመለት ሸክሟን የሚሸከምላት ትፈልጋለች ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሀገር ለማዳን ስንሠራ በሀገር ላይ ተጨማሪ ቁስል ለማምጣት የሚሠሩ አሉ፣ ተሸንፈው መቅረታቸው ግን አይቀሬ ነው፣ ማጥፋት ማዳንን አያሸንፈውምና ሲሉም ገልጸዋል።

ሀገርን ለማዳን የምንሠራቸው ሥራዎች ብርሃናቸው ቦግ ብሎ ዛሬ ላይበራ ይችላል፡፡ ለሁሉም እኩል ላይታዩ ይችላሉ፡፡ ካለፈው የችግር ጊዜ እየወጣን መሆኑ፣ ወደ አዲስ ሀገራዊ ሁኔታ እየተሻገርን መሆኑ ለጊዜው ላይታወቅ ይችላል፡፡ ከጥምቀት በኋላ ለሁሉ እንደተገለጠው፣ የኢትዮጵያ ትንሣኤና ሕዳሴ ለሁሉም ግልጽ የሚሆንት ጊዜ ይመጣል ሲሉ በመልዕክታቸው አመላክተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button