ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: በኢትዮጵያ የበልግ ዝናብ በሚያስከትለው ጎርፍ ሳቢያ ከአንድ ሚሊየን በላዩ ሰዎች ከቀያቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ ሲል የመንግስታቱ ድርጅት አስጠነቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 19/2016 ዓ.ም፡- በተያዘው የበልግ ወራት የሚኖረው ከፍተኛ ዝናብ በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች የጎርፍ አደጋ እንዲከሰት ያደርጋል ሲል የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው ሪፖርት አመላከተ።

በኢትዮጵያ በበልግ ዝናብ በሚያስከትለው ጎርፍ ሳቢያ አንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን (1898000) ሰዎች ተጠቂ ይሆናሉ ያለው ቢሮው  ከነዚህ ውስጥም ከአንድ ሚሊየን በላዩ ይፈናቀላሉ ሲል ገልጿል።

የአደጋ ስጋት ኮሚሽን እና የሰብአዊ ረድኤት ድርጅቶች በቀጣይ ቀሪ የበልግ ግዜያት በጎርፍ ሳቢያ ሊፈናቀሉ የሚችሉ ሰዎችን ለማገዝ የሚያስችል እቅድ መውጣቱን ማስተባበሪያ ቢሮው ጠቁሟል።

ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥማቸው ይችላል የተለዩ ቦታዎች መኖራቸውን የጠቆመው ቢሮው በተለይም በአፋር፣ አማራ፣ ሶማሌ እና ደቡብ ክልሎች ላይ መሆናቸውነ አስታውቋል።

የድጋፍ እጥረት ምክንያት የሚያስፈለጉ እርዳታዎች እንዳይሟሉ እንቅፋት መሆኑን ገልጿለ።

በሶማሌ ክልል ብቻ በጎርፍ ሳቢያ አንድ ነጥብ ሁለት ሚሊየን ዜጎች ተጠቂ ይሆናሉ ያለው ቢሮው 773ሺ የክልሉ ነዋሪዎች ከቀያቸው ሊፈናቀሉ ይችላሉ ብሏል። በአፍዴር፣ ሊበን፣ ቆራሄ ኤረር፣ ዳዋ፣ ጃራር፣ ኖጎቦ እና ሸበሌ ዞኖች ከተለዩ ቦታዎች መካከል መሆናቸውነ ጠቁሟል።

በደቡብ ክልል 145ሺ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ተጠቂ ይሆናሉ ያለው ቢሮው ከነዚህ ውስጥ 64ሺ የሚሆኑት ከቀያቸው መፈናቀላቸው አይቀርም ብሏል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በኦሮምያ ክልል ደግሞ 421ሺ ዜጎች በጎርፍ አደጋ ተጋላጭ ናቸው ያለው የቢሮው ሪፖርት 104ሺ ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ጠቁሟል።  

በአፋር ክልል ደግሞ 83ሺ ሰዎች የጎርፍ ተጠቂ ይሆናሉ፣ ከነዚህ ውስጥም 61ሺዎቹ ሊፈናቀሉ ይችላሉ ብሏል።

በአማራ ክልል 45ሺ ሰዎች በጎርፍ ይጠቃሉ ከነዚህ ውስጥም ሶስት ሺ የሚሆኑት ሊፈናቀሉ ይችላሉ ሲል ገልጿል።

በትግራይ ክልል ጎርፍ ሊያጠቃቸው የሚችለው ሰዎች ቁጥር አራት ሺ ይደርሳል ያለው ቢሮወ ከነዚህ ውስጥ አንድ ሺ የሚሆኑት ሊፈናቀሉ ይችላሉ ሲል ጠቁሟለ።

እስካሁን በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ጎርፈ መከሰቱን እና ጉዳት ማድረሱን የተመለከቱ መረጃዎች መውጣታቸውነ አመላክቷል።

በሌላ ዜና ከየካቲው እስከ ሚያዚያ ወራት እንደ አዲስ በተቀሰቀሰው የአፋር እና ሶማሌ ኢሳ ጎሳ አባላት መካከል የሚደረገው ግጭት በርካታ የሁለቱም ጎሳ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውነ የመንግስታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ በሪፖርቱ አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button