ዜና

ዜና: ከአልሸባብ ጋር ተቀላቅለው የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ እስከ 12 ዓመት በሚደርስ እስራት ተቀጡ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11/2016 ዓ.ም፡- የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ድሬዳዋ ምድብ 4ኛ ወንጀል ጅግጅጋ ተዘዋዋሪ ችሎት ከአልሸባብ የሽብር ቡድን ጋር ተቀላቅለው የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ ነበር የተባሉ ስምንት ግለሰቦች እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ።

የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ተከሳሾች ሀሰን ኢብራሂም (ሀፎ)፣ አማን(ሳለሃዲን) ቃሲም፣ ጂብሪል (ነስረዲን) ራሻ፣ አብዱልሀኪም (ዘይድ) ሁሴን፣ ተማም (ሀምዛ) ሼህ አብዶ፣ አብዲ ጣሂር ኮሌ፣ አደን ሰላድ ካድየ እና መአሊ ድሬ ጉሬ እንደሚባሉ ተጠቁሟል።

ተከሳሾቹ በኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት፣ በክልሉ የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መርማሪዎች ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመሆን ምርመራ ሲያከናውን እንደነበር ይታወሳል።

ተከሳሾቹ መቀመጫውን ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ያደረገው የአልሸባብ ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድን አባል በመሆን ስልጠና በመውሰድ፣ ህዝብን በማሸበር መንግስትን ለማስገደድ የተሰጣቸውን ተልዕኮ ተቀብለው በ2014 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ በሶማሌ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ተግባር በመፈጸም እና የሽብር ቡድኑን በመደገፍ እንዲሁም መረጃ በማቀበል ተሳትፎ እንዳላቸው በዝርዝር አስፍሯል።

በጥር 5 ቀን 2015 ዓ.ም በነበረ ቀጠሮ በችሎት የክስ ዝርዝሩ በንባብ ተሰምቶ ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን ክደው የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ የሰነድ ማስረጃዎችንና የሰው ምስክሮችን በተለያዩ ቀናቶች በችሎት አቅርቦ አሰምቷል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ ተከሳሾቹ በተከሰሱበት ድንጋጌ እንዲከላከሉ ብይን ቢሰጥም ተከሳሾቹ መከላከያ ማስረጃ የለንም በማለት አቤቱታ ማቅረባቸውን ተከትሎ የመከላከያ ማስረጃ የማቅረብ መብታቸው ታልፎ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ከዚህም በኋላ ፍርድ ቤቱ የዐቃቤ ሕግ የቅጣት ማክበጃ አስተያየትን እና የተከሳሾቹን የቅጣት ማቅለያ አስተያየትን በመያዝ በአንደኛ መዝገብ ሀሰን ኢብራሂም (ሀፎ) የተባለ ተከሳሽን በ11 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ ሲሆን÷ 3ኛ፣ 4ኛ፣ 5ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች ደግሞ እያንዳንዳቸው በ12 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ በሙሉ ድምጽ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በሁለተኛው መዝገብ ማለትም ለአልሸባብ የሽብር ቡድን መረጃ በማቀበል የሽብር ተግባር ጥፋተኛ የተባሉት አብዲ ኮሌ፣ ጣሂር፣ አደን ሰላድ ካድየ እና ሙአሊ ድሬ ጉሬ የተባሉ ተከሳሾን ደግሞ እያንዳንዳቸውን በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ መስጠቱን ከፋና ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በወቅቱ አልሸባብ በሶማሌ ክልል በኩል ሰርጎ በመግባት የሽብር ጥቃት ለመፈጸም ቢሞክርም እንሰዳልተሳካለት እና ወደ ክልሉ ሰርጎ የገባው የአልሸባብ የሽብር ቡድን ስጋት በማይሆንበት ደረጃ በፀጥታ ኃይሎች መደምሰሱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሁመድ ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

ርዕሰ መስተዳደር  ሙስጠፌ ሙሁመድ እንዳሉት፤ የአልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሌ ክልል ጠረፋማ አካባቢዎች ጥቃት ለመሰንዘር ሞክሯል።

ቡድኑ በክልሉ ነዳጅ በሚገኘበት አካባቢ ለመንቀሳቀስ መሞከሩን ጠቅሰው፤ በአፍዴር ዞን በኩል ወደ መሀል ሀገር ለመግባት ያደረገው ሙከራ ባለበት መቀጨቱን አስረድተዋል።

የሽብር ቡድኑ እንቅስቃሴ ስብጥር ካሁን ቀደሙ የተለየ ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ፤ በሀገሪቱ ውስጥ ሙጃሂዲን የተባለ የሸኔ እና አልሸባብ የምስራቅ አፍሪካ ቀጣናን የማሸበር ተልዕኮ ተሰጥቶት የተላከ እንደሆነ ገልጸዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button