ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና: “የኦነጉ በቴ ኡርጌሳ ግድያ በገለልተኛ ወገን ሊጣራ ይገባዋል” የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአሜሪካ ሴኔት ውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ ኦነግ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3/2016 ዓ.ም፡- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ ሚያዚያ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት በ ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ በጥይት ተመተው መገደላቸውን ተከትሎ በርካታ ተቋማት እና ግለሰቦች ግድያቸው በገለልተኛ አካል እንዲጣራ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች የላይኛው ምክር ቤት ሴኔት የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ባወጡት መግለጫ ግድያው አስደንጋጭ እና በጣም የሚያበሳጭ ነው ሲሉ ገልጸው የመንግስት ባለስልጣናት በግድያው ዙሪያ ታማኝነት ያለው፣ ገለልተኛ አለም አቀፍ አካል እንዲያጣራው ማድረግ ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል።

በኦሮምያ ከህግ አግባብ ውጭ የሚደረጉ ግድያዎች፣ የፖለቲካ ጭቆና የተለመዱ ተግባራ ሁነዋል ሲሉ ገልጸዋል።

የጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አገዛዝ የፖለቲካ ተቃዋሞዎችን፣ መገናኛ ብዙሃንን እና ተቃዋሚዎችን በኦሮምያ ብቻ ሳይሆን በመላ ሀገሪቱ እያፈነ ይገኛል ሲሉ ኮንነዋል። ይህም በመላ ሀገሪቱ አለመራጋጋት እና የጸጥታ እጦት እንዲከሰት አድርጓል ሲሉ ገልጸዋል። 

የጭቆና ፖሊሲን የሚያራምዱ እና አላግባብ ስልጣናቸውን የሚጠቀሙ አካላትን እንዲጋላጡ እና ለድርጊታቸው ተጠያቂ የማድረጊያ ጊዜው አልረፈደም ብለዋል።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮው በኩል ባወጣው መግለጫ በግድያው ዙሪያ ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ ጠይቋል። ፍትህ እና ተጠያቂነት የሀይል መጠቀም አዙሪት እንዲያበቃ ለማድረግ ወሳኝ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ ግድያውን የፈጸሙ ግለሰቦች ተጠያቂ ለማድረግ የሚያስችል ምርመራ የፌደራል መንግስቱ እና የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት ማከናወን ይገባቸዋል ሲል አሳስቧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከግድያው ጋር በተገናኘ ባወጣው መግለጫ ድርጊቱን በጽኑ አውግዞ ገለልተኛ እና ነጻ ምርመራ እንዲከናወን ጠይቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button