ዕለታዊፍሬዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዕላታዊ ዜና፡ በኢትዮጵያ ከ1500 በላይ የሙስና ጥቆማዎች መቀረባቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5/ 2015 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያ ከ1500 በላይ ሙስናን የተመለከቱ ጥቆማዎች መቅረባቸውን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈጻሚ ፈርዳ ገመዳ፤ በ2016 በጀት ዓመት እስካሁን ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 1451 ሙስናን የተመለከቱ ጥቆማዎች መቅረባቸውን ለኢፕድ ተናግረዋል።

ከፌዴራል ተቋማት በቀጥታ ለኮሚሽኑ ከደረሱት 80 የሙስናን ጥቆማዎች መካከል 65ቱን ጥቆማዎችና መረጃዎቹን ለፌዴራል ፖሊስ አሳልፎ በመስጠት የማጣራት ሥራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡ ለክልል የሚደርሱ የሙስና ጉዳዮች ወደ ኮሚሽኑ ሳይደርሱ ከክልሉ የሕግ አካላት ጋር በመሆን እንዲመረመሩ ይደረጋልም ብለዋል። 

ወደ ኮሚሽኑ መረጃ ክፍል ከሙስና ጥቆማዎች በተጨማሪ የተለያዩ የመልካም አስተዳደርና ሌሎች ቅሬታዎች እንደሚመጡ ጠቁመው፤ በዚህም ኮሚሽኑ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 265 ቅሬታዎችን ተቀብሎ ጉዳዩ ወደሚመለከታቸው አካላት መምራቱን አስረድተዋል።

ወደ ኮሚሽኑ የሚመጡ ጥቆማዎች ሁሉም የተረጋገጡ የሙስና ወንጀሎች ናቸው ማለት እንደማይቻልና አንዳንዶች ያለምንም ማስረጃ የግል ፀብን በመያዝ የሚቀርቡም ይኖራሉ ብለዋል፡፡

አቶ ፈርዳ እንዳመለከቱት፤ በሀገሪቱ የሙስና ፈጻሚዎች ጉዳይ አሁንም አሳሳቢ መሆኑን በየጊዜው እየተሠሩ ያሉ ጥናቶች ስለሚጠቁሙ ህብረተሰቡ ከሙስና ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለመስጠት ያለው ተባባሪነት ሊጠናከር ይገባል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button