ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በዋግ ኽምራ ዞን ድርቅ ባስከተለው የኩፍኝ ወረርሽኝ የ15 ህፃናት ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14/ 2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ድርቅ ባስከተለው የኩፍኝ ወረርሽኝ  የ15 ህፃናት ህይወት ማለፉን የአስተዳደሩ ጤና መምሪያ ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቀ። 

የአስተዳደሩ ጤና መምሪያ ኃላፊ አሰፋ ነጋሽ “ዞኑ እጅግ ውስብስብ የህብረተሰብ ጤና ችግር ያለበት” መሆኑን ገልጸው፤ በአጠቃላይ 1800 የሚጠጉ ሰዎች በኩፍኝ በሽታ ተጠቅተዋል ብለዋል።

በዞኑ በ2015 ያጋጠመው የዝናብ እጥረት ያስከተለውን ድርቅ ተከትሎ፤ ኮሌራ፣ ኩፍኝ፣ ወባ፣ እከክ እና ከእንሰሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ በሽታ መከሰቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የወባ በሽታም እየተስፋፋ መሆኑን የገለጹት ኃላፊው፤ በዋናነት ግን የኩፍኝ በሽታ “አስጊ ደረጃ” መድረሱን ተናገረዋል።

በጥቅምት ወር በሳሃላ ወረዳ ተከስቶ ወደ ሁሉም ወረዳዎች መስፋፋቱን የተገለጸው የኩፍኝ በሽታ በስፋት ህጻናትን እያጠቃ መሆኑንና በ70ዎቹ የሚገኙ አረጋውያንም በበሽታው መጠቃታቸውን አሰፋ ገልጸዋል።

በተከሰተው መግብ እጥረት ምክንያት በበሽታዎች የሚጠቁ ህጻናት፣ ነፈሰ ጡርና አጥቢ እናቶች ቁጥር እየጨመረ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

ድርቁ ካስተለው የምግብ እጥረት በተጨማሪ ለሶስት አመታት በዘለቀው ጦርነት ምክንያት በዞኑ የክትባት አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ ባለመቻሉ ወረርሽኑ እንዲስፋፋ ምክንያት መሆኑን ጤና መምሪያ ኃላፊው ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር በድርቁ ለተጎዳው ማህበረሰብ ምላሽ ለመስጠት የሚያስፈልገው ምግብና ግብዓቶች እየገባ ባለመሆኑ ወረርሽኑ እንዲስፋፋና ሞት እንዲከሰት አድርጓል ብለዋል። 

“እንደ አበርገሌ፣ ጻግብጅ፣ ዳና ጅብራ ያሉ ወረዳዎች ላይ በጸጥታ ምክንያት መድኃኒቶች ለማድረስ፣ ተንቀሳቅሶ ለመስራት፣ ባለሙያዎችን ለማስለጠን የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ እንቅፋት ሆኗል፤ በዚህ ምክንያት ምላሽ ለመስጠት ባለመቻሉ ህጻናት ሞተዋል”ሲሉ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኃላፊው አክለውም፤ ወቅቱ ክርምት በመሆኑና በአካባቢው የሚድርስ ምርት ባለመኖሩ፤ በዞኑ ያለው የምግብ እጥረት እንደሚስፋፋና ሁኔታዎች ፈታኝ እንደሚሆኑ ጠቁመዋል።

በተከሰተው ድርቅ በሰሃላ ወረዳ በረሃብ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ከ10 ሺህ በላይ የቤት እንስሳት መሞታቸውን፣ የዞኑ የምግብ ዋስትናና አደጋ መከላከል ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ምረት መላኩ በህዳር ወር ለአዲስ ስታንዳርድ መግለጻቸው ይታወሳል

በወረዳው ረኀብ ያስከተለው ጉዳቱ ተባብሶ በመቀጠሉ፣ ባለፈው ሳምንት በቢላዛ ቀበሌ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የቀበሌው አስተዳደር ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም አምስት ሺሕ እንስሳት መሞታቸውን አመልክቷል፡፡

አስቸኳይ የምግብ ርዳታ የሚያስፈልጋቸው ከ46ሺሕ በላይ ሰዎች በወረዳው መኖራቸውን የገለጹት ዋና አስተዳዳሪው፣ ለተጎጂዎች የእርዳታ እህል የሚያጏጉዙ ተሽከርካሪዎች በጸጥታው ችግር ምክንያት ወደ አካባቢው ለመምጣት ፈቃደኛ አለመኾናቸው፣ እንዲሁም የተሰበረው የተከዜ ድልድይ አለመጠገኑ፣ ችግሩን አባብሶታል ብለዋል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button