ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ

ዕለታዊ ዜና፡ በክልሉ የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የኑሮ ውድነቱን የመቀነስ ሥራን አስተጓጉሏል _ የአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 3/2016 ዓ ም፦ በአማራ ክልል የተፈጠረው የሰላም መደፍረስ የኑሮ ውድነቱን የመቀነስ ሥራን ማስተጓጎሉን የክልሉ ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ አስታወቀ። ይህም በዓለም ላይ ከተከሰተው የሸቀጦች ዋጋ መናር ጋር ተጨማምሮ የኑሮ ውድነቱ በክልሉ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ መኾኑን የቢሮ ምክትል ኀላፊ ፈንታው ፈጠነ ገልጸዋል።

“የሰላም መደፍረስ በንግድ ሥርዓቱ ላይ ብልሹ አሠራሮች እንዲፈጠሩ አድርጓል፤ ሕገ-ወጥ ኬላ እና ቀረጥ አንዱ ማሳያ ነው” ብለዋል፡፡ በየቦታው የተፈጠሩ ሕገ-ወጥ ኬላዎች በምርት አቅርቦትና ግብይት ላይ ችግሮች እንዲከሰቱ እያደረጉ መኾኑንም አብራርተዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል፡፡

አቶ ፈንታው፣ እየተባባሰ የመጣውን የኑሮ ውድነት ለማስተካከል በክልሉ ሰላምን ማስፈን እና ነጻ የምርት ዝውውር መፍጠር እንደሚያስፈልግ  አንስተዋል፡፡ በክልሉ ሰላም እንዲሰፍን ሁሉም ጥረት ማድረግ እንዳለበት ኀላፊው ፈንታው ፈጠነ ገልጸዋል።

አማራ ክልል የሀገሪቱን 40 በመቶ ምርት የሚሸፍን ቢሆንም ምርቱ ከሚመረትበት ቀበሌ እና ወረዳ ወደ ትላልቅ ከተሞች ነጻ የምርት ዝውውር ባለመኖሩ የኑሮ ውድነቱ አርሶ አደሩን ጨምሮ በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደሩ የኅብረተሰብ ክፍልችን እየፈተነ ይገኛል ብለዋል፡፡

የኑሮ ውድነቱ አሁን ካለበት የባሰ እንዳይኾን በክልሉ ዘላቂ ሰላም ማስፈን፣ የግብርና ምርቶችን ማሳደግ እና ነጻ የኾነ የምርት ዝውውር ሥርዓትን በማስፈን ረገድ ሁሉም ባለድርሻ ሊሠራ ይገባል ብለዋል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button