ፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ ሳዑዲ አረብያ ድንበሯን አቋርጠው ሊገቡ በሞከሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ ፈጽማለች ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች ኮነነ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 15/2015 ዓ.ም፡- የሳዑዲ አረብያ ድንበር ጠባቂዎች በየመን በኩል ድንበሯን አቋርጠው ሊገቡ የሞከሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንን መግደላቸውን ሂዩማን ራይትስ ዎች ባወጣው ሪፖርት አስታወቀ። በየመን በኩል ወደ ሳዑዲ አረበያ ሊገቡ የነበሩ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከየካቲት ወር 2014 ዓ.ም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም ድረስ በሳኡዲ አረብያ ድንበር ጠባቂዎች በኩል በተከፈተባቸው ተኩስ መገደላቸውን ያስታወቀው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋሙ ሂዩማን ራይት ዎች ድርጊቱ በሰብአዊነት ላይ ተፈጸመ ወንጀል ነው ሲል ኮንኗል።

የሳኢዲ አረብያ መንግስት ከተቀረው አለም በተደበቀ መልኩ በርካታ ሴቶች እና ህጻናትን እየገደለ ባለበት ሁኔታ ለገጽታ ግንባታ በሚል በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር በስፖርቱ አለም እያፈሰሰ ይገኛል ሲል ተችቷል። የሳኡዲ አረብያ መንግስት ስደተኞችን እና ጥገኝነትን በሚፈልጉ ሰዎች ላይ ገዳይ መሳሪያ መጠቀም የሚፈቅድ ማንኛውንም ፖሊሲዎቿን እንድታስወግድ ተቋሙ ጠይቋል።

ጉዳዩ የሚያሳስባቸው ሀገራት ተጠያቂነትን ለማስፈን ጫና እንዲፈጥሩ የጠየቀው ሂዩማን ራይት ዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉዳዩን እንዲያጣራ ጠይቋል።

አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪው ተቋም ሂዩማን ራይት ዎች ይፋ ባደረገው ሪፖርት እንዳስታወቀው የሳኡዲ አረብያ ድንበር ጠባቂዎች በየመን በኩል ድንበር አቋርጠው ሊገቡ የሚሞክሩ ስደተኞች ላይ ከፍተኛ ፍንዳታ የሚፈጥሩ መሳሪያዎችን እንደሚጠቀሙ እና በቅርብ እርቀት ላይም የሚገኙትንም ተኩሰው እንደሚገድሉ አመላክቷል።  

በአንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ድንበር ጠባቂዎቹ የትኛውን የሰውነት አካልህ ቢመታ ይሻለሃል እያሉ በመጠየቅ በቅርብ እርቀት ላይ ሁነው ተኩሰው አካላቸውን እንደሚያጎድሉት ሂዩማን ራይት ዎች በሪፖርቱ አካቷል።

750ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በሳኡዲ አረብያ ተሰደው እንደሚገኙ ሪፖርቱ ጠቁሟል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button