ዜናፖለቲካህግ እና ፍትህ

ዜና፡ በመቐለ ሊደረግ ከታቀደው ሰልፍ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የባይቶና መሪ የሆኑት ኪዳነ አመነ እና ተስፋሚካዔል ንጉስን በቁጥጥር ስር አዋለ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 1/ 2015 ዓ.ም፡- በትግራይ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በነገው እለት በመቐለ ሊያደረጉ ካቀዱት የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ፖሊስ የብሄራዊ ባይቶ ዓባይ (ባይቶና) መሪ እና የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት ኪዳነ አመነ እና ተስፋሚካዔል ንጉስን መሰሩ ተገለፀ፡፡

የኪዳነ እና ተስፋሚካኤል እስር የተሰማው ከሰልፉ ጋር በተያያዘ ቀደም ብለው የታሰሩ አባላቶች እንዲፈቱላቸው በመጠየቅ ላይ የነበሩ እና ለእስር የተዳረጉት የሳልሳይ ወያነ ሊቀመንበር ሃያሉ ጎዲፋይ፣ የባይቶና ዓባይ ትግራይ ከፍተኛ አመራር አቶ ክብሮም በርሀ እና የውድብ ናፅነት ትግራይ ሊቀመንበር ዶ/ር ደጀን በርሀ ከሶስት ሰዓታት በእስር ላይ መለቀቃቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ፖሊስ ኪዳነን እና ተስፋሚካኤልን ዛሬ ጠዋት ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ስለ ተቃውሞ ሰልፉ ውይይት አድርገው ከቢሮአቸው አጠገብ መንገድ ላይ በነበሩበት ወቅት ነው ሲል የውድብ ናፅነት ትግራይ ተቃዋሚ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር እና የውጭ ጉዳይ ሀላፊ የሆኑት አቶ አለምሰገድ አረጋይ ተናግረዋል።

በትግራይ የሚገኙ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተከታታይ ከጳጉሜ 2 አስከ 4 /2015 ዓ.ም በመቐለ ከተማ የአደባባይ የተቋወሞ ስልፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ የመቐለ ከተማ አስተዳደር የተመረጠው ጊዜ አዲስ አመትና ሃይማኖታዊ በዓላት የሚበዙበት በመሆኑ ለማስተናገድ የማይመች ነው ሲል መከልከሉ የታወሳል። በተጨማሪም በበዓሉ በሚኖረው የህዝብና የመኪና ሰፊ እንቅስቃሴ ምክንያት በሚፈጠር የስራ መደራረብ ምክንያት ሰልፉን ማካሄድ ለማካሄድ እንደማይቻል የከተማ አስተዳደሩ ገልጧል።

ይህንን ተከትሎ ሶስቱ ፓርቲዎች ለከተማ አስተዳደሩ መግለጫ ነሃሴ 26 ቀን በሰጡት ምላሽ ሰላማዊ ሰልፉ በዓልን ምክንያት በማድረግ ማስፈፀም አንችልም ማለታችሁ ውድቅና የማንቀበለው ነው ብለዋል። ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊውን ህዝባችን ይዘን በያዝነው የግዜ ሰሌዳ ሰልፉን እንደምናካሂደው ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን ሲሉም ገልፀው ቅስቀሳዎች ሲያደርጉ ተስተውለዋል፡፡

አቶ አለምሰገድ ሰልፉን ማከናወን የተፈለገው በትግራይ ፍትህ፣ ሰላም እና ፀጥታ እንዲረጋገጥ ለመጠየቅ ነው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ የቀድሞ ተዋጊዎች የምስክር ወረቀትና መልሶ ማቋቋም እንዲደረግላቸው እና ሁሉን አካታች የሆነ አስተዳደር እንዲመሰረት ለመጠየቅ ያለመ ሰልፍ መሆኑን አቶ አለምሰገድ ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይህ በእንዲህ እያለ ከፓርቲዎቹ አንዱ የነበረው ዓሲምባ ከተጠራው ሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፍ ራሱን ማግለሉ አስታወቋል። የፓርቲው ሊቀምነበር አቶ ዶሪ አስገዶምና በፓርቲው በማህበራዊ የትስስር ገፅ በተሰራጨው መረጃ  “የተጠራው ሰልፍ ህጋዊ አካሄድ ያልተከተለ እንደሆነ የሚመለከታቸው አካላት በማስረጃ አስደግፈው አስረድተውናል፤ ህግ ይከበር እያልን ህግ መጣስ ህዝባችንን ስለማይመጥን ከተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ራሳችን ለማግለል ወስነናል። ሁሉም ከህግ በታች ነው ” ሰሊ ፓርቲው ተሳታፊ አለመሆኑን አስታውቀዋል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button